ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ሩሲያና ዩክሬን በገቡበት ጦርነት ሳቢያ ሊከሰት የሚችለውን ሰብዓዊ ቀውስ ለመቋቋም ያግዛል በማለት የግብርና እና የአርብቶ አደር ውጤቶች ለውጭ ገበያ እንዳይዉሉ ወሰነች
ታይም የዜና ምንጭ እንደዘገበው በግብርና ምርቶች ለዓለም አቀፍ የምግብ ዋስትና ተደራሽነት ከፍተኛ ሚና ያላት ዩክሬን በወቅታዊው ጦርነት ሳቢያ ምርቶች ለየትኛውም ሀገር እንዳይቀርቡ አሳስባለች።
ስንዴ፣ አጃ፣ ማሽላ፣ ስኳር፣ የቁም እንስሳትና ተዋፅኦዎቻቸውን ጨምሮ ለምግብነት የሚያገለግሉ በርካታ ምርቶችን ነው የዩክሬን የግብርና እና የምግብ ፖሊሲ ሚኒስቴር ያገደው።
ይህ ውሳኔ ከዩክሬን ምርቶችን የሚያስገቡ የአውሮፓ፣ እስያ እና የአፍሪካ ሀገራት ላይ ከፍተኛ ጫና ያሳድራል ተብሎ ተሰግቷል።
ስንዴ ለውጭ ገበያ በማቅረብ ከዓለም አምስተኛ ደረጃን የያዘችው ዩክሬን እ.ኤ.አ በ2019 ከ3 ቢልየን ዶላር በላይ በውጪ ንግድ ከስንዴ ማግኘት ችላለች።
ግብፅ፣ ኢንዶኔዥያ፣ ቱርክ እና ቱኒዝያ ደግሞ ዋነኛ የዩክሬን ስንዴ ደንበኞች ናቸው። ኢትዮጵያም ከዩክሬን ከፍተኛ የስንዴ ግዢ ከሚፈፅሙ ሀገራት አንዷ ስትሆን በ 2018 የ43 ሚልየን ዶላር ስንዴ ገዝታለች።