ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የጀርመን ቅርንጫፍ በሁለት ዓመት አንዴ የሚሰጠውን የሰብዓዊ መብት ሽልማት ዘንድሮ ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) እንደሰጠ አስታውቋል።
ኢሰመጉ በኢትዮጵያ ለሰብዓዊ መብቶች መከበር ለ30 ዓመታት ላደረገው ጉልህ አስተዋጽኦ ነው የድርጅቱን የ10 ሺህ ዩሮ የገንዘብ ሽልማት ያሸነፈው። ኢሰመጉ ለሰብዓዊ መብቶች መከበር የሚታገለው በከፍተኛ አደጋ ውስጥ ሆኖ እንደሆነ ሸላሚው ድርጅት ገልጦ፣ በተለይ በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት የኢሰመጉ ሚና የማይተካ እንደሆነ ጠቁሟል።