ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኢትዮጵያ የምግብ ዘይት አምራቾች ማኅበር ለውጭ ገበያ በሚቀርበው የቦሎቄ ምርት ላይ መንግሥት ቢያንስ ላንድ ዓመት እገዳ እንዲጥል ለንግድ እና ቀጠናዊ ትብብር ሚንስቴር ጥያቄ ማቅረቡን ሪፖርተር ዘግቧል።
ማኅበሩ እገዳው እንዲጣል የጠየቀው፣ ቦሎቄ ለውጭ ገበያ መቅረቡ በአገር ውስጥ የምግብ ዘይት እጥረትን አባብሷል በማለት ነው። የአገር ውስጥ የምግይ ዘይት አምራቾች በአማካይ በዓመት 2.4 ሚሊዮን ኩንታል ቦሎቄ እንደሚያስፈልጋቸው ማኅበሩ ገልጧል።
የምግብ ዘይት ፋብሪካዎች ግን በቦሎቄ እጥረት ሳቢያ አሁን እየተጠቀሙ ያሉት 25 በመቶ የማምረት አቅማቸውን ብቻ ነው። አምራቾች ቦሎቄ ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ ድርጅት መግዛታቸው ቀርቶ በቀጥታ ከገበሬዎች መግዛት ይፈልጋሉ።