ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ወዳጆቻችን እናመሰግናለን ያለው የዩክሬን ኤምባሲ ወረራውን የፈፀመችው ሩስያ በሁሉም ዩክሬናውያን ከተሸነፈች በኃላ ኤምባሲው ቁርጠኛ ለሆኑ የፌስቡክ ወዶጆቹ ወደ ዩክሬን ከክፍያ ነፃ የመግቢያ ቪዛ ሎተሪ ዕድል ሊሰጥ እያሰበ መሆኑን አሳውቋል።
ኤምባሲው እስከዛሬ ንቁ የሆኑ የፌስቡክ አክቲቪስቶች ብሎ የ38 (ኢትዮጵያውያን) ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል።
ከቀናት በፊት በአዲስ አበባ የሚገኘው የሩስያ ኤምባሲ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ ለሩስያ ድጋፋቸውን የሚገልፁ በየዕለቱ ብዙ ደብዳቤዎች በመቶዎች የሚቆጠር አስተያየት እንደሚደርሰው ገልጾ ሀገሮቻችን በችግር ጊዜ በመደጋገፍ እና በመረዳዳት እንደዚህ አይነት ጠንካራ ረጅም ጊዜ የሚቆይ፣ ወዳጃዊ ግንኙነት ስላላቸው ኩራት ይሰማናል ” ማለቱ አይዘነጋም።
ኢትዮጵያውያን ተከታዮቹ እያሳዩት ላለው ድጋፍና ከሩስያ ጎን እንደሚቆሙ መምረጣቸውን በእጅጉ እንደሚያደንቅ መግለፁ ይታወሳል።
ይህን የሩስያ ኤምባሲ መልዕክት ተከትሎ በአዲስ አበባ የፖላንድ እና የጀርመን ኤምባሲዎች የሩስያን ኤምባሲ የሚቃወም ጠንካራ መልዕክቶችን ማስተላለፋቸው ይታወቃል።