ኢትዮጵያ ነገ ዜና || አቶ ዳውድ ዛሬ ረፋድ ላይ ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር ስብሰባ ለመቀመጥ ወደ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አምርተው እንደነበር ቢቢሲ ዘግቧል።
ምርጫ ቦርድ ከቀናት በፊት የኦነግ የረጅም ጊዜ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ አንድ ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ ከቤታቸው እንዳይወጡ ተከልክለው በቁም እስር ላይ እንደቆዩ ባደረገው ማጣራት ማረጋገጡን ገልጾ ነበር።
ይህም ድርጊት ከሕግ ውጪ መሆኑን በመጥቀስ በሊቀ መንበሩ ላይ የተጣለው የመንቀሳቀስ ገደብ በአፋጣኝ እንዲነሳ ቦርዱ ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን እና ለብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት በደብዳቤ መጠየቁ ይታወሳል።
ከአቶ ዳውድ የቁም እስር በተጨማሪ በርካታ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች በእስር ላይ ይገኛሉ።
የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት የሆኑት አቶ ሚካኤል ቦረን እና አዮ ኬነሳ አያና ጭምሮ የኦነግ ከፍተኛ አመራሮች የሆኑት አቶ ዳዊት አብደታ እና አቶ ለሚ ቤኛ አሁንም በእስር ላይ እንደሚገኙ ቢቢሲ በዘግቧ።