150 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት ከውጭ እንዲገባ ተወሰነ 

150 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት ከውጭ እንዲገባ ተወሰነ 

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኑሮ ውድነትን ለማሻሻልና ገበያውን ለማረጋጋት በሚቀጥሉት ሶስት ወራት 150 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት ከውጭ እንዲገባ መወሰኑን የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ አህመድ ሸዴ ገለጹ።

ሚኒስትሩ ዛሬ በጽ/ቤታቸው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ መንግስት የኑሮ ወድነትን ለማሻሻልና የገበያ ዋጋን ለማረጋጋት ተከታታይነት ያለው እርምጃ ይወስዳል ማለታቸዉም ተሰምቷል።

በአሁኑ ጊዜም 12.5 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት ወደ ሀገር ውስጥ እየገባ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 4.8 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ወደ ሀገር ውስጥ ገብቶ ለህብረተሰቡ እየተከፋፋለ ሲሆን 7.7 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ደግሞ በሚቀጥሉት ሶስት ሳምንታት ውስጥ ወደ ሀገር ውስጥ ተጠቃሎ እንደሚገባ ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡፡

ድፍድፍ ዘይት ከውጭ አስመጥተው በሀገር ውስጥ ለሚያመርቱ ሶስት ፋብሪካዎችም ምርቶቻቸውን ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያቀርቡ የውጭ ምንዛሬ የተመቻቻላቸው መሆኑንና አእጥረቱን በዘላቂነት ለመፍታት ለሌሎች አቅራቢዎችም ዘይት ከውጭ አስመጥተው ለመንግስት እንዲሸጡ ፈቃድ የተሰጣቸው መሆኑንም አቶ አህመድ መገለጻቸው ተነግሯል፡፡

ባለፉት ሁለትና ሶስት አመታት መንግስት የምግብ ዘይት ከቀረጥ ነጻ እንዲገባ በማድረጉ 23.7 ቢሊዮን ብር ያጣ ሲሆን ለነዳጅ የ100 ቢሊዮን ብር ድጎማ አድርጓል ነዉ የተባለዉ፡፡

LEAVE A REPLY