ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በሥነ-ምግባራቸው ፖሊስን የማይመጥኑና ጥፋት አጥፍተዋል የተባሉ 146 የፖሊስ አባላትና አመራሮችን ከሥራ መሰናበታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ባለፉት 6 ወራት ያከናወናቸውን የወንጀል መከላከልና ምርምራ ተግባራትን አፈፃፀም አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።
የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲካ ፈንታ እንድገለፁት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በከተማዋ የሚፈፀሙ የወንጀል ተግባራትን በግማሽ ዓመቱ በ15 በመቶ የመቀነስ እቅድ ቢኖረውም ማሳካት የተቻለዉ አምስት በመቶ ብቻ ነው።
ባልፉት ስድስት ወራት በተደረገ ፍተሻና ብርበራ ስምንት የመትረይስ ጥይቶችን ጨምሮ ከ28 ሺህ በላይ የተለያዩ የጦር መሳሪያ ጥይቶች ተይዘዋል።
በተጨማሪም ፈንጂዎችና ቦንቦችን ጨምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ የወታደራዊ መገልገያዎች በአዲስ አበባ የተለያዩ ስፍራዎች ተጥለው መገኘታቸውን ተነግሯል።