ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ተወልደ ገ/ማርያም ከኃላፊነታቸው በፈቃዳቸው መልቀቃቸው ተገለፀ።
ዋና ሥራ አስፈፃሚው ከኃላፊነታቸው በይፋዊ መንገድ የለቀቁት ከጤናቸው ሁኔታ ጋር በተገናኘ እንደሆነ ታማኝ ምንጮች ነግረውኛል ሲል ኢትዮ ንግድና ኢንስትመንት መድረክ ዘግቧል፡፡
ከስድስት ወራት ላለፈ ጊዜም ህክምናቸውን በአሜሪካ እየተከታተሉ እንደሚገኙም ተገልጿል፡፡ ተወልደ ገ/ማርያም አየር መንገዱን በዋና ሥራ አስፈፃሚ አሥፈፃሚነት የመሩ ሲሆን፤ ለ37 ዓመታትም አየር መንገዱን አገልግለዋል፡፡