የኦፌኮ ስለኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ድርድር ጠየቀ – ሼኔ አላለም

የኦፌኮ ስለኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ድርድር ጠየቀ – ሼኔ አላለም

ኢትዮጵያ ነገ ዜና ||  የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ፓርቲ (ኦፌኮ) የሰሜኑን ጦርነት ለማስቆም እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን ላይ ያለውን አድናቆት በመግለፅ የፌደራል መንግስቱ የሰላም እጁን ለትግራይ ክልል እንደዘረጋ ሁሉ ከኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ጋር የገባበትን ጦርነት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ቁርጠኛ አቋም ላይ ሳይዘገይ እንዲደርስ አናሳስባለን ብሏል።

ፓርቲው ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄዱን ተከትሎ ባወጣው የአቋም መግለጫ መንግስት የእርስ በእርስ ጦርነቱ ላይ እየተሳተፉ ከሚገኙ ታጣቂ ኃይሎች ጋር በመደራደር ግጭቶችን ማስቆም እንዳለበት ገልጿል።
በተጨማሪም፣ ተስፋ ተጥሎበት የነበረው “የለውጥ ሂደት ተቀልብሶ ወደ ዲሞክራሲ ሊደረግ የነበረው የሽግግር እድል በመባከኑ ምክንያት ወደ ተስፋ መቁረጥ፣ የእርስ በእርስ ጦርነትና የሀገር መፍረስ አደጋ የተጋረጠብን መሆኑ በጣም አሳዝኖናል” ብሏል ፓርቲው።

ብሔራዊ ምክክር ለማድረግም፣ ዘላቂ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረስ፣ ሁሉም የፖለቲካ እስረኞችን መፍታት፣ ከታጣቂ ኃይሎች ጋር መደራደር፣ የምክክሩን ሂደት ገለልተኛ ማድረግ እና የተፈናቃዮችን ህይወት መታደግ ይገባል በማለት ፓርቲው የመፍትሄ አቅጣጫ ያላቸውን አስቀምጧል።

LEAVE A REPLY