በሀገር ውስጥ የዲ ኤን ኤ ምርመራ ሊጀመር መሆኑ ተገለጸ

በሀገር ውስጥ የዲ ኤን ኤ ምርመራ ሊጀመር መሆኑ ተገለጸ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ከዚህ ቀደም ወደ ዉጭ ሀገር በመላክ ይሰጥ የነበረዉን አገልግሎት በሀገር ዉስጥ ለመስጠት ያስችላል የተባለለት ለወንጀል ምርመራ የሚያግዝ የዘረ-መል (ዲ ኤን ኤ) ምርመራ በሀገር ዉስጥ ለመጀመር መዘጋጀቱን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።

አገልግሎቱ በአንድ ወር ጊዜ ዉስጥ ስለሚጀምረዉ ቴክኖሎጂው አተገባበር እና ስለሙከራው ውጤታማነት በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ ለህዝብ መረጃ እንደሚሰጥ የፌደራል ፖሊስ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ጄላን ኢብራሂምን ተናግረዋል።

ለወንጀል ምርመራ ስራ የሚያግዙ አዳዲስ የፎረንሲክ ምርመራ ማሽኖችን ወደ ሀገር አስገብቶ ጥቅም ላይ እያዋለ መሆኑን የገለጸዉ ፖሊስ ሌሎች አሰራሮቹንም በቴክኖሎጂ እያዘመነ እንደሚገኝ ዳይሬክተሩ ነግረዉናል።

ከዚህ በተጨማሪም የአቪየሽን ፖሊስ፣ የምድር ባቡር ፖሊስ፣ የዩኒቨርሲቲ ደህንነት ፖሊስ እንዲሁም በኢንዱስትሪ እና ቱሪዝም ላይ ትኩረት አድርጎ የሚከታተል የፖሊስ ክፍሎች በአዲስ መልክ ተደራጅተዋል ነዉ የተባለው።

LEAVE A REPLY