ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ከመጋቢት 23 ቀን 2014 ጀምሮ ለሀይማኖት ተቋማት የብሮድካስት ፈቃድ መስጠት እንደሚጀመር የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር መሀመድ እድሪስ አስታወቁ።
በ2012 ማጠናቀቂያ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ፀድቆ፤ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ሥራ ላይ የዋለው የመገናኛ ብዙሃን ፖሊሲ የሀይማኖት ድርጅቶች ከሬዲዮ ሞገድ በስተቀር በሌሎች ማሰራጫ ዘዴዎች ፈቃድ አግኝተው አስተምህሮታቸውን ለተከታያቸዉ ማድረስ እንደሚችሉ አቅጣጫ ማስቀመጡን ተከትሎ፤ ባለስልጣኑ ፈቃድ መስጠት መጀመሩ ዋና ዳይሬክተሩ አስረድተዋል።
ቀደም ብሎ የነበረው የብሮድካስት አዋጅ ለሀይማኖት ድርጅቶች የብሮድካስት አገልግሎት ፈቃድ መስጠትን ይከለክል እንደነበር ይታወሳል።