ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በቀድሞ የኦነግ ሊቀመንበር ገላሣ ዲልቦ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ “ገላሣን ያጣናቸው ይበልጥ በሚያስፈልጉን ጊዜ ነው ብለዋል
የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በበኩላቸው በገላሣ ዲልቦ እረፍት የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀዋል።ርዕሰ መስተዳድሩ በሀዘን መግለጫቸው “ኦሮሚያ ጠንካራ ሰው አጥታለች” ብለዋል።
“ገላሣ ዲልቦ የኦሮሞ ነፃነት ታጋይ ነበሩ” ያሉት ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ ሙሉ ህይወታቸውን ለኦሮሞ ሕዝብ የገበሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።በሀዘን መግለጫቸው ለኦሮሞ ሕዝብ በሙሉ ብርታትን እመኛለሁ ብለዋል።
ኦቦ ገላሳ ዲልቦ የ1983 ሽግግር ወቅትን ጨምሮ ለረጅም ጊዜ የኦነግ ሊቀመንበር ሆነው አገልግለዋል፡፡