ምርጫ ቦርድ የኦሮሞ ነጻነት ንቅናቄ ፓርቲን ለጊዜው ማገዱን አሳወቀ 

ምርጫ ቦርድ የኦሮሞ ነጻነት ንቅናቄ ፓርቲን ለጊዜው ማገዱን አሳወቀ 

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ቦርዱ ፓርቲውን ለጊዜው ያገደው፣ ፓርቲው መጋቢት 15 አካሄድኩት ባለው ጠቅላላ ጉባዔ ለቦርዱ ያቀረባቸው የ634 ጉባዔተኞችን ስም ዝርዝር እና ፊርማ የያዙ ሰነዶች አጠራጣሪ በመሆናቸው ለምርመራ ወደ ፌደራል ፖሊስ እንደላካቸው በመግለጽ ነው።

በፓርቲው ጠቅላላ ጉባዔ ላይ በታዛቢነት የተወከሉ ሁለት የቦርዱ ተወካዮች የጉባዔተኞቹ ብዛት 250 ብቻ እንደነበር ማረጋገጣቸውን ቦርዱ ገልጿል። በቦርዱ ሕግ መሠረት የአንድ አገር ዓቀፍ ፓርቲ ጠቅላላ ጉባዔ ማካሄድ የሚችለው 500 አባላቱ ከተገኙለት ብቻ ነው።

LEAVE A REPLY