HR6600/S3199 ህግ ሆኖ እንዲፀድቅ የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ እንዲዘገይ ተወሰነ

HR6600/S3199 ህግ ሆኖ እንዲፀድቅ የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ እንዲዘገይ ተወሰነ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በአሜሪካ ኮንግረስ እና ሴኔት #HR6600/S3199 ህግ ሆኖ እንዲፀድቅ የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ እንዲዘገይ ወሰነ።

ረቂቅ ህጎቹ እንዳይፀድቁ በተለያዩ የአለም ክፍሎች የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የተለያዩ ጥረቶችን ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወቃል።
በመጨረሻም የአሜሪካ ኮንግረስ እና ሴኔት ረቂቅ ህጉ እንዲቆይ የሚያስችል ሥምምነት ላይ ደርሷል።

የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መንግስት በተለያዩ ምክንያቶች ከህዘብ ጋር ቅራኔ እየፈጠረ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን የወሳኔ ሃሳቡ እንዲዘገይ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የምእራባዉያን መንግሥታት ጋር ያለውን ታማኝነት ለማሣየት የሚያደረገው ጥረት ያስገኘው ውጤት መሆኑን ተንታኞች ይገልጻሉ። መንግሰት እያደረገ ያለው የዲፕሎማሲ ጥረት የተንሸዋረረ እና የኢትዮጵያዊያንን ጥቅም አሳልፎ የሚሰጥ መሆኑን የሚገልፁ በረካታ ኢትዮጵያውያንን እያሳሰበ ነው።

HR 6600 በኢትዮጰያ እየተደረጉ ያሉ የእርዳታ እንቅሰቃሴዎች እንዲገደቡ ከማደረጉም  በላይ ኢትዮጵያ የጦር መሪያ ገዥዎችን እንዳታደርግ የሚከለክል ነው።

አሁንም የአሜሪካ መንግሰት ይሀንን አፋኝ ህግ እንደዘገይ አደርገው እንጂ ህጉ ከኢትዮጰያ መንግሥተ ጋር ያለው ግንኙነት በሻከረ ቁጥር እንደገና ሊያነሳው እንደሚችል የፖለቲካ ተንታኞች ይናገራሉ።

LEAVE A REPLY