የብልጽግና አመራሮች ለሀገር ስጋት ሆነዋል” ሲል ኢዜማ አሰታወቀ

የብልጽግና አመራሮች ለሀገር ስጋት ሆነዋል” ሲል ኢዜማ አሰታወቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ገዢው ብልፅግና ፓርቲ ህብረ ብሔራዊ ነኝ ይበል እንጂ ብሔር ተኮር ፓርቲ መሆኑን አረጋግጧል ሲል ኢዜማ ገለፀ።

ፓርቲው ዛሬ ሚያዝያ 6 ቀን 2014 ዓ.ም. ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ በላከው መግለጫ የሕዝብን አብሮ መኖር በቋሚነት በመሸርሸር የመንደራቸው ‹አውራ› ለመሆን የሚታትሩ የብልፅግና አመራሮች ከዚህ አስነዋሪ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ አሳስቧል ክልሎችን ለመምራት በመንበሩ የተቀመጡ የብልፅግና አመራሮች መሽቶ በነጋ ቁጥር እርስ በእርስ እየተናከሱ አለፍ ሲልም ለፀብ እየተጋበዙ ከኑሮ ውድነቱ በላይ ራሳቸው አመራሮቹ ለሀገር ስጋት ሆነዋል” ሲል የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ገለፀ።

መግለጫውን በንባብ ያቀረቡት ይመስገን መሳፍንት ገዢው ብልፅግና ፓርቲ ህብረ ብሔራዊ ነኝ ይበል እንጂ ብሔር ተኮር ፓርቲ መሆኑን አረጋግጧ ብለዋል። ለእያንዳንዱ ድርጊታቸው ተጠያቂ እንደሚሆኑ ሊያወቁ ይገባል።” ሲሉ አሳስበዋል።

የዜጎችን ደህንነት በተመለከተም የደቡብ ኦሞ እና የኮንሶ ዞኖችን ጉዳይ የኢዜማ መግለጫ ጠቅሷል።

የንጹሃን ዜጎች ሕይወት እንደዋዛ ለመቀጠፉ፣ አካል ለመጉደሉ እንዲሁም ሃብትና ንብረታቸው ለመውደሙ የጸጥታ ችግር ቅድመ ትንበያ የሚሠራው መንግሥታዊ አካል ደካማ ወይንም ቸልተኛ በመሆኑ ነው ሲል ፓርቲው ገልጿል።

ኢዜማ መንግስት የዋጋ ግሽበቱን ከሚያባብሱ ተግባራቱ እንዲቆጠብ፣ የከተማ መሬት ወረራ እና የቤቶች ልማት ችግር በፍጥነት እንዲፈታ፣ ከሀይማኖት ጋር የሚያያዙ ችግሮች ቅድሚያ እንዲሰጣቸው ጥሪ አቅርቧል።

LEAVE A REPLY