ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ድጋፉ በአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅት (ዩ ኤስ ኤይድ) በኩል በአማራ፣ አፋር እና ትግራይ ክልሎች በግጭቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የሚሰራጭ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የተደረገው ድጋፍ አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ለመድረስ፣ የጤና ተቋማት የሚሰጡትን አገልግሎት ለማሻሻል ፣ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል ፣ የጾታ ጥቃቶችን እና የሥነ ልቦና ችግሮችን ለመቀነስ ይውላልም ተብሏል፡፡
አሜሪካ በቀጣይ የችግር ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ለመርዳት ቁርጠኛ መሆኗ የተገለጸ ሲሆን ÷ ለዚህም የሰብዓዊ እርዳታ ድርጅቶች በአማራ፣ አፋር እና ትግራይ ክልሎች ችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች የሚያደርጉትን የሰብዓዊ ድጋፍ አጠናክረው መቀጠላቸው ተጠቁሟል፡፡
ዩናይትድ ስቴትስ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ግጭት ከተቀሰቀሰ ጀምሮ እስካሁን 995 ሚሊየን ዶላር የሚወጣ የሰብዓዊ ድጋፍ ማድረጓንም ዩ ኤስ ኤይድ ጉዳዩን አስመልከቶ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡