ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ስድስት የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ቅርንጫፍ ሠራተኞች በወንጀል ተጠርጥረው በክልሉ የጸጥታ ኃይሎች ትላንት ሚያዚያ 21ቀን 2014 ዓም በቁጥጥር ስር ውለው መታሰራቸው ሪፖርተር ዘግቧል።
ቅርንጫፍ መስሪያቤቶቹ በአዳማ፣ ነቀምት፣ ጅማ፣ ጊምቢ፣ በደሌ፣ መቱ ሲሆኑ ሁሉም መታሸጋቸው ታውቋል።
የቅርንጫፍ ሠራተኞቹ በቁጥጥር ስር መዋላቸውንና መታሰራቸውን የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ለሪፖርተር ያረጋገጠ ቢሆንም የታሰሩትን ሠራተኞች ብዛትና የታሰሩበትን ቦታ ከመግለጽ ተቆጥቧል ተብሏል።