ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል አሙዲ (ሞሃ) የለስላሳ መጠጥ ኢንዱስትሪ የለስላሳ መጠጦችን ማምረት እንዳቆመ ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል።
ሚሪንዳ፣ ፔፕሲ፣ ሰበን አፕ፣ ኩል የተፈጥሮ ማዕድን ውሃ ያሉ መጠጦችን በማምረት የሚታወቀው ሞሃ አሁን ላይ የማምረት ሂደቱን አቁሟል። የካፒታል ጋዜጣ ምንጮች እንደሚጠቁሙት ኩባንያው ምርቱን ለማቆም የተገደደው ለምርቶቹ የሚሆን ጥሬ ዕቃዎች እጥረት ስላጋጠመው ነው።
ከጥቂት ወራት በፊት ጀምሮ ኩባንያው በጥሬ ዕቃ እጥረት እና በውጭ ምንዛሬ እጦት ሳቢያ ከአቅሙ በታች በሳምንት ሦስት ቀን እየሠራ የነበር ቢሆንም አሁን ባለው ሁኔታ ግን ለስላሳ መጠጥ ድርጅቱ ካለፉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ ስራውን ሙሉ በሙሉ ማቆሙ ነው የተነገረው። ችግሩ እስኪስተካከል ድረስ ሰራተኞችም ዕረፍት እንዲወስዱ መደረጋቸው ተገልጿል ።