ሳፋሪኮም ለኢትዮጵያ ቅርንጫፉ 2 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ሊሰጥ መሆኑ ተገለፀ

ሳፋሪኮም ለኢትዮጵያ ቅርንጫፉ 2 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ሊሰጥ መሆኑ ተገለፀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ የሚገኘውን ቅርንጫፍ መስርያ ቤቱን ለመደገፍ ከልማት ፋይናንስ ተቋማት፣ ከሀገር ውስጥ ባንኮች፣ እና ከመሳሪያ አቅራቢዎች ወደ 2 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ለመሰብሰብ ማቀዱን አስታውቋል።

በ2022/2023 የበጀት አመት ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ለሚገኘው ቅርንጫፉ የሚያወጣው ወጪ ከ60 እስከ 65 ቢሊዮን የኬንያ ሽልንግ ሊደርስ እንደሚችል ስለሚጠበቅ ድጋፉን ማሰባሰቡ አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱ ተጠቅሷል።

ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ለመስራት የሚያስችለውን የቴሌኮም ፍቃድ ለማግኘት የሚሆን ሲስተም ለመዘርጋት ባሳለፍነው አመት ብቻ የ400 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ማውጣቱን መግለጹ የሚታወስ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎት ለመስጠት እ.ኤ.አ ከሐምሌ 9 2021 ጀምሮ የሚቆጠር የመሥሪያ ፍቃድ ማግኘቱ ይታወቃል።

ኩባንያው በኢትዮጵያ ለሚጀምረው የቴሌኮም አገልግሎት ብድር አዘግይቶበት ከነበረው የአሜሪካው ዓለማቀፍ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን ጋር እንደገና ውይይት መጀመሩን ሰሞኑን ባወጣው ዓመታዊ የፋይናንስ ሪፖርት መግለጹም ይታወሳል።

LEAVE A REPLY