ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ከሶስት ቀናት በፊት አዲስ አበባ ላይ የተሰወሩት ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ በባህር ዳር ከተማ ዘጠነኛ ፖሊስ ጣቢያ እንደሚገኙ ተገለፀ።
ቢቢሲ አማርኛ የተፈራ ማሞ ባለቤትን ምንጭ አድርጎ እንደዘገበው የጀነራሉ ጠበቃ እና የሚያውቋቸው ሰዎች ባህር ዳር እንደሚገኙ እና ደህና መሆናቸውን የሚገልጽ መልዕክት ደርሷቸዋል።
ቢቢሲ በዘገባው የክልሉን የፀጥታና ደህንነት አካላት አስተያየት ለማካተት ሙከራ አድርጎ እንዳልተሳካለት ገልጿል።
የቀድሞ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥ የሆኑት ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ ሰኞ ግንቦት 8 ቀን 2014 ዓ.ም. ረፋድ ላይ ከአቶ ዮሐንስ ቧያለው ጋር ለመገናኘት ከቤታቸው ከወጡ በኋላ መሰወራቸው ይታወሳል።