የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኃላፊዎች በሙስና ተከሰሱ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኃላፊዎች በሙስና ተከሰሱ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ ኃላፊ ሆኖ ሲሰራ ከደንበኞች የማይንቀሳቀስ ሂሳብ ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ስለመውሰዱ የሚያስረዳ ማስረጃ የተገኘበት ግለሰብ ክስ ተመሰረተበት።

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የባንኪንግ ቢዝነስ መኮንን ሆነው ሲሰሩ የነበሩ ሶስት የባንኩ ሰራተኞችም በዚሁ መዝገብ ክስ ተመስርቶባቸዋል።

1ኛ ተከሳሽ የባንኪንግ ቢዝነስ መኮንን የሆኑት አቶ እስጢፋኖስ ሙሉጌታ ገቢሳ () 2ኛ ተከሳሽ ወ/ሮ አስኩዋል ወልደአብዝጊ 3ኛ ተከሳሽ በቀለ ሽፌ 4ኛ ተከሳሽ ይልቃል አዳነ ናቸው የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል ሲል በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዐቃቤ ህግ ዳይሬክቶሬት ጄነራል ክስ የመሰረተባቸው።

አንደኛ ተከሳሽ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ” ፒኮክ መናፈሻ ቅርንጫፍ ” ተቀዳሚ ባንኪንግ ቢዝነስ መኮንን የሥራ ኃላፊ ሆኖ ሲሰራ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ በባንኩ ደንበኛ ከሆኑ ግለሰቦች ሳይንቀሳቀስ በመቆየታቸው ምክንያት የማይንቀሳቀሱ ሂሳብ (Inactive) የነበሩ የቁጠባ ሂሳቦች ሃላፊነቱን በመጠቀም ወደ ተንቀሳቃሽ ሂሳብ (Active) በመቀየር ደንበኞች ከሂሳባቸው ጋር ለሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ያስተሳሰሩትን ስልክ ቁጥር ሲስተም ላይ የተቀየረውን በማፅደቅ ከደንበኞች ሂሳብ ላይ በተለያዩ ጊዚያት በራሱ ሥም በተከፈቱ የሂሳብ ቁጥሮች በአጠቃላይ ብር 2,535,000 (ሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ሰላሳ አምስት ሺ) ብር በሞባይል ባንኪንግ በማስተላለፍ ወስዷ በማለት ከፍትህ ሚንስትር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

LEAVE A REPLY