ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በዋግ ኽምራ አለም አቀፍ የረድኤት ድርጅቶች አፋጣኝ እርዳታ ካላደረጉ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወት ሊያልፍ እንደሚችል ተገለጸ
በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ስር የሚገኙ 4 ወረዳዎች በአሸባሪው የህወኃት ቡድን እጅ ስር በመሆኑ ነዋሪዎች ከፍተኛ ችግር ውስጥ ናቸው ሲሉ የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር የኮሚኒኬሽን መምሪያ ሀላፊ አቶ ከፍያለው ደባሱ ተናግረዋል፡፡
በአበርገሌ ወረዳ፣ባግብጂ ወረዳ፣ ዝቋላ፣ ሰቋጣ ወረዳ አካባቢዎች አሸባሪው የህወኃት ቡድን በስፋት የሚንቀሳቀስበት በመሆኑ ተፈናቃዮች ምን አይነት ሁኔታ ውስጥ እንዳሉ ማወቅ ባለመቻሉ በችግር ውስጥ በመሆናቸው አፋጣኝ እርምጃ እንደሚያሻቸው ተገልፆል፡፡
በየእለቱ የተፈናቃዮች ቁጥር እየጨመረ ሲሆን አሁን ላይ በዞኑ ከ88 ሺበላይ ተፈናቃዮች እንደሚገኙ ተጠቁሟል፡፡አለም አቀፍ የረድኤት ድርጅቶች በተለያዩ ክልሎች ገብተው እርዳታ እንደሚያደርጉት ሁሉ በነዚህ አራት ወረዳች ገብተው አፋጣኝ እርዳታ ካላደረጉ በብዙ ሺ የሚቆጠር ህዝብ ልናጣ እንችላለብ ሲሉ አቶ ከፍያለው ደባሱ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡