መንግስት ህጋዊ እርምጃ ባለመወሰዱ የእገታ  ወንጀል ተባብሷል ሲል ኢሰመጉ አስታወቀ

መንግስት ህጋዊ እርምጃ ባለመወሰዱ የእገታ  ወንጀል ተባብሷል ሲል ኢሰመጉ አስታወቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የህግ ስርዓትን ያልተከተለ እስር እና አስገድዶ መሰወር ወይም እገታን በተመለከተ መንግስት ውትወታ ቢደርሰውም የሚታይ እርምጃ አለመወሰዱ ወንጀሉ እንዲባባስ በር ከፍቷል ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) አስታወቀ።

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በኢትዮጵያ ውስጥ የጋዜጠኞች፣ ተፎካካሪ ፓርቲ አባላት፣ የማህበረሰብ አንቂዎች እንዲሁም የተለያዩ ህብረተሰቦች ላይ ተደጋጋሚ ህገ ወጥ እስር እየተፈፀመ መሆኑንም ጉባኤው አሳስቧል።

ኢሰመጉ ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው ከእስር በዋስ የተለቀቀው ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ በድጋሚ ከመኖሪያ ቤቱ መወሰዱ ቢሰማም ቤተሰቦቹ እና ጠበቃው እስካሁን ያለበትን ማወቅ አልቻሉም ብሏል። በተጨማሪም የደረሰበት ሳይታወቅ አንድ ሳምንት የሞላው ገጣሚ እና የማህበረሰብ አንቂ በላይ በቀለ ወያም እስካሁንምያለበት አለመታወቁን ኢሰመጉ አረጋግጧል።

አሁንም የቀጠሉት እገታና ህግን ያልተከተለ እስር ለሰብዓዊ መብት ጥሰት የተመቻቹ በመሆናቸው መንግስት ሰብዓዊ መብቶችን የማክበርና የማስከበር ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ አቅርቧል።

LEAVE A REPLY