ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የታለመለት የነዳጅ ድጎማ አሠራርን በተመለከተ ቁጥጥር የሚያደርጉ ሁለት ሺህ ተቆጣጣሪዎች መሠማራታቸውን የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታወቀ።
የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን የነዳጅ አቅርቦት፣ ስርጭት፣ ክትትልና ቁጥጥር ዳይሬክተር ዴሬሳ ኮቱ በተለይም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳስታወቁት፤ ባለስልጣኑ ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ የታለመለት የነዳጅ ድጎማ አሠራርን የሚቆጣጠሩ ሰዎችን አሰልጥኗል።
ሰልጣኞቹም የነዳጅ ድጎማ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ከሆነበት ሰኔ 29 ቀን 2014 ጀምሮ በተለያዩ አካባቢዎች ቁጥጥር የማድረግ ሥራቸውን ጀምረዋል ብለዋል።
ከሁለት ሺህ ተቆጣጣሪዎች ውስጥ 70ዎቹ በአዲስ አበባ ከተማ መሰማራቸውን የገለጹት ፤ በመላ አገሪቷ በአጠቃላይ በዘጠኝ ክላስተር የተከፋፈሉ ተቆጣጣሪዎች በተለያዩ ከተማዋና ወረዳዎች ጭምር ተመድበው እየሠሩ መሆኑን ተናግረዋል።