“ከደሙ ንጹህ ነኝ” ልንባል እንችላለን || ግርማ ካሳ

“ከደሙ ንጹህ ነኝ” ልንባል እንችላለን || ግርማ ካሳ

ሃንጋሳ አህመድ ኢብራሂም ፣ ” እየመጣን ነዉ !! በአብዛኛዉ ዜጎቻችን ዘንድ በሁሉም ነገሮች ላይ የነገሮች ብዥታዋች ነበሩ። ዛሬ ፀሀይ ወገግ ብላለች። ከምዕራብ እስከ ሰሜን ፣ ከምሥራቅ እስከ ደቡብ ሁሉም እኩል ተረድቶታል። እዉነትና ፅንስ እያደረ ይታያል መባሉ በጥንቱም ያሌ ነዉ። ምስጋና ለፈጣሪያችን ይሁንና በዝህ ብረሐን ዉስጥ በቅርቡ እንመጣለን። ከዚህ በኃላ ያለዉ አካሄድ ለጥ ያለ ነዉ” የሚል ጦማር በማህበራዊ ገጹ ለጥፏል፡፡ ሃንጋሳ በሃረርጌ ክፍለ ሃገር ባለ የምርጫ ወረዳ ተመርጦ ፣ የፓርላማ አባል የሆነ ወንድም ነው፡፡

ታዬ ደንድዓም ተመሳሳይ ይዘት ያለው መልእክት ነው ያጋራን፡፡ ” ከጥሞና በኋላ!
ጥሞና መልካም ነዉ:: ነገሮችን በጥልቀት ለመስማትና ለመመዘን ዕድል ይሰጣል:: በቂ ጊዜ ወስዴን ብዙ አዳምጠናል:: አሁን ግራ-ቀኙን በሚገባ ተረድተን መዝነናል:: ለውሳኔ ለመገናኘት ቀጠሮ ይዘናል! በቅርቡ ይጠብቁ” ሲል አንድ የሚናገረው፣ የሚገልጸው ነገር እንዳለ ነው የጠቆመው፡፡

ታዬ፣ ሃንጋሳም አንድ የሚታወቁበት ነገር ቢኖር በኦሮሞ ክልል መንግስት አመራር ላይ፣ በተለይም በሺመልስ አብዲሳ ላይ ከፍተኛ ችግር ያለባቸው፣ ተቃውሞ የሚያሰሙ መሆናቸውን ነው፡፡ ለዚህም ብዙ ወገኖች አድናቆት ችረዋቸዋል፡፡

አንድ በትልቅ ልብ መባል ያለበት ነገር ግን አለ፡፡ እነዚህ ወገኖች የኦሮሞ ክልል መንግስትንና ሺመልስ አብዲሳ ላይ ቅሬታዎች ሲያቀርቡ፣ በአራት ኪሎ የተቀመጠው አብይ አህመድ ላይ ግን አንዲት ቃል ተንፍሰው አያውቁም፡፡
ሺመልስ አብዲሳ ያለ አብይ አህመድ ፍቃድና እውቅና በራሱ ችግር እየፈጠረ ያለ ይመስል፡፡ ለምን ብሎ መጠየቅ አስፈላጊ ነው፡፡

የውስጥ አዋቂዎች በተደጋጋሚ እንደሚናገሩት፣ ከሺመልስ አብዲሳና ከአዳነች አበቤ ወዘተ ጀርባ ያለው አብይ አህመድ ራሱ ነው፡፡ “አንተ ይሄን አድርግ፣ አንቺ እንዲህ በይ፣ እኔ ይሄን አደርጋለሁ” ተባብለው፣ ተመካክረው፣ አቅደውና ተናበው ነው በጋራ እየሰሩ ያሉት፡፡

አሁን አሁን ግ ን አብይ አህመድ ከፍተኛ ጫና እየመጣበት በመሆኑ፣ ስልጣኑን ለማስቀጠል፣ አብረዉት የሰሩትን የመስዋት በግ አድርጎ ለማቅረብ ያቀደ ይመስለኛል፡፡ እነ አቶ ለማ መገርሳን፣ እነ አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን፣ እነ አቶ ንጉሱ ጥላሁንን ፣ እንደ ማስቲካ አኝኮ ተጠቅሞባችው እንደተፋቸው፣ እንደካዳቸው፣ በራሱ የፖለቲካ ስህተቶች ለተፈጠሩ ችግሮች፣ የርሱን መመሪያ ተቀብለው ሲሰሩ የነበሩትን አዳነች አበቤንና ሺመልስ አብዲሳ አጋልጦ ሊሰጥ ያሰበ ነው የሚመስለው፡፡ ለሆነው ነገር እነርሱ ላይ አላኮ፣ “እኔ አይደለሁም፣ የአዲስ አበባ መስተዳደር ነው፣ የኦሮሞ ክልል መንግስት ነው…” እያለ፣ ከደሙ ንጹህ እንደሆነ አድርጎ በማቅረብ፣ በማታለል በስልጣኑ ለመቀጠል አስቦ፡፡ ለዚህም ደግሞ እነ ሃንጋሳንና ታዬ ደንድዓን እንደ መሳሪያ ሊጠቀምባቸው የተዘጋጀ ነው የሚመስለው፡፡

ወገኖች፣ ኢትዮጵያ ውስጥ እየሆነ ላለው ነገር ፣ ትልቁ ችግር አዳነች አበቤ አይደለችም፡፡ ሺመልስ አብዲሳም አይደለም፡፡ እነ ደብረ ጽዮን አይደሉም፡፡ ዳዎድ ኢብሳ ወይንም ጃል መሮ አይደሉም፡፡ ሸኔ የሚባሉትም አይደሉም፡፡

ትልቁ ችግር ፣ የአገርን ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ ሃላፊነት ያለበት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ችግሮች ባሉበት ቦታ ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ የማድረግ ስራዎች መስራት አለመቻሉ ነው፡፡ አለመቻሉ ብቻ ሳይሆን በብዙ ቦታዎችም ራሱ ጠቅላይሚኒስትርነት ቦታ ላይ የተቀመጠው የችግሩ ጠንሳሽና ጠማቂ መሆኑ ነው፡፡ በአጭሩ አነጋገር የአገር ትልቁ ችግር ራሱ አብይ አህመድ ነው፡፡

አንዳንድ ወገኖች የአገር ችግር የዘር ፖለቲክው ነው ይላሉ፡፡ አዎን የዘር ፖለቲካው ነው፡፡ ግ ን የዘር ፖለቲካውን የመቀየር አቀም ያለው የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ የተቀመጠው ማን ነው ? አብይ አህመድ አይደለም እንዴ ? አገር ከዘር ፖለቲካ እንዳትወጣ በፌዴራል መንግስት ደረጃ አንቆ የያዘው አብይ አሀመድ አይደለም እንዴ ? ይኸው ስልጣን ከያዘ አምስት አመት ሞላው፣ የዘር መካረሩ፣ በኃይለማሪያም ደሳለኝ ዘመን ከነበረው በመቶ እጥፍ አልጨመረምን ?

በተለያዩ ጊዜ “የአዲስ አበባ ህዝብ ኦሮሞን ይጠላል” እያለ በአዲስ አበባና በኦሮሞ ማህበረሰብ መካከል፣ “የትግራይ ህዝብ ደጀናችን አይደለም፣ ወግቶናል” እያለ በትግራይና በተቀረው ኢትዮጵያዊ መካከል ልዩነቱና መቃቃእር እንዲፈጠር አላደረገም ወይ ? ኦርቶዶስክ ቤተ ክርስትያን በኦሮምኛ አገልግሎት እንደምትሰጥ እያወቀ፣ “ኦሮሞ በኦሮምኛ አገልግሎት እንዲሰጠው ይፈለጋል” ብሎ የኦርቶዶስክ ቤተ ክርስቲያን በዘር ለመከፋፈል ጦርነት አልከፈተም ወይ ? ሌላ መጻፍ እስኪሰለች አብይ አህመድ የዘር ካርድ በመምዘዝ፣ በኢትዮጵያዉያንን መካከል መቀራረብ እንዳይኖኢር ያደርገ፣ በውሸት፣ በማታለል፣ በመከፋፈል፣ በዘረኝነት፣ በጥላቻና በእብሪት ላይ የተመሰረተ ፖለቲካ የሚያራምድ ሰው ነው፡፡

ባይገርማችሁ ለኦሮሞ ብልጽግ ናዎች አንድ ነገር ይናገርና፣ ለአማር ብልጽግ ናዎች ሌላ ነገር ይላቸዋል፡፡ በኦሮሞ ብልጽግና ውስጥ ከፋፍሏቸው፣ ለአንዱ ወገን አንድ ነገር ያላል፤ ለሌላው ሌላ ነገር ያላል፡፡ ሁሉንም እያባላ፣ እርሱ ከላይ ሆኖ እንደ “መል ዓክ፣ እንድ አስታራቂ፣ እንደ ተረጋጋና አስተዋይ መፍትሄ አመንጭ አድርጎ ያቀርባል፡፡

ወገኖች ይህ ሰው በጣም አደገኛ ነው፡፡ በቶሎ መነሳት አለበት፡፡ እርሱ ከተነሳ ፣ አዳነች አበቤን በነጋትው የአዲስ አበበ ምክር ቤት ተሰብስቦ ያነሳታል፡፡ እርሱ ከተነሳ፣ ብርሃኑ ጁላና ደመላሽ ገብረሚካኤል እንዲለቁ ተደርጎ፣ በመከላከያና በፌዴራል ፖሊስ አዲስ አመራር ይተካል፡፡ ያኔ ወለጋ በሉ የትም ያሉ ችግሮችን በሳምንታት ውስጥ ማስተካከል ይቻላል፡፡ እነ ጃል መሮ አርፈው ይቀመጣሉ፡፡ አሁን እኮ ያ ሁሉ ችግር ያለው መከላከያና የፌዴራል ፖሊስ አቅም ስለሌላቸው ነው፡፡ አቅም የሌላቸው ደግሞ ካላቸው አመራር የተነሳ ነው፡፡ አመራር ከተቀየረ፣ ፌዴራል ፖሊስ፣ መከላከያ ስራቸውን በትክክል ይሰራሉ፡፡

LEAVE A REPLY