ኢትዮጵያ በእንግሊዝ ለሽያጭ የቀረበ ጋሻ ጨረታ እንዲሰረዝ ጠየቀች

ኢትዮጵያ በእንግሊዝ ለሽያጭ የቀረበ ጋሻ ጨረታ እንዲሰረዝ ጠየቀች

ኢትዮጵያ ነገ ዜና :- አንደርሰን እና ጋርላንድ፣ የተባለ ጥንታዊ ቅርሶችን የሚሰበስብ ኩባንያ የመቅደላ ጦርነት ወቅት በእንግሊዝ ጦር ወደ እንግሊዝ የተወሰደ ጥንታዊ ጋሻ ለመሽጥ የወጣ ጨረታ እንዲሰረዝ ኢትዮጵያ ጠየቀች።

በየካቲት 29ቀን2024 የሚካሄደውን “የጥንታዊ ጋሻ ጨረታ” እንዲሠረዝ የጠየቀው የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ጋሻው  ለእውነተኛ ባለንብረቱ ለኢትዬጵያ ህዝብና መንግስት  ሊመለስ ይገባዋል ሲል አሳስቦል።

ይህ በአጫራች ድርጅቱ ለሽያጭ የቀረበው ጋሻ ከአቢሲኒያ  “ማግዳላ ኤፕሪል 13 ቀን 1868” በሚል ጽሑፍ የተቀረጸበት ሲሆን የእንግሊዝ ጦር መቅደላ ላይ ከአፄ ቴድሮስ ጋር  የተዋጋበትን ቀን ጊዜ ያመለክታል።

aይህው ጋሻ ለአለፉት 150 አመታት የመቅደላው ጦርነት የእንግሊዝ ጦር አዛዥ የነበረው የጄኔራል የሮበርት ኮርኔሊስ ናፒየር ቤተስብ ንብረት ሆኖ መቆየቱ ታውቋል ።

የኢትዮጵያ መንግስት ለአጫራቹ ኩባንያ በፃፈው ደብዳቤ በኢትዬጵያ ቅርስን መጠበቅና ማስተዳደር  የሚመለከተው  ባለስልጣን ስም .. ጋሻውን ለመሽጥ የወጣውን ጨረታውን እንድትሰርዙ አጥብቀን እንጠይቃለን እና ይህ የተዘረፈ እቃ  ወደ  በህጋዊ መንገድ ለባለቤቶቹ እንዲመለሱ ሻጮችን በማነጋገር ፣  የኢትዮጵያ መንግስት ቅርስን ለማስመለስ እንደሚሰራ እስታውቁል።

LEAVE A REPLY