ኬንያ የኢትዮጵያና የሶማሊያ መሪዎችን ልታደራድር ነው!!

ኬንያ የኢትዮጵያና የሶማሊያ መሪዎችን ልታደራድር ነው!!

ኢትዮጵያ ነገ ዜና:- በአሁኑ ወቅት በናይሮቢ የኬኒያ መንግስት እንግዳ ሆነው የሚገኙትን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትርና የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ከቅርብጊዚ ወዲህ በመካከላቸው የተፈጠረውን አለመግባባት በውይይቱ እንዲፈቱ የኬኒያው ፕሬዚዳንት ሊያደራድሩዋቸው እንደሆነ በስፋት እየተነገረ ነው።

የካቲት16ቀን 2024 በኬኒያ መንግስት በተደረገላቸው ግብዣ ኬኒያን በኦፊሴል እየጎበኙ ያሉት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በበርካታ ጉዶዬች ከኬንያው ፕሬዚዳንት ጋር ከተወያዩ በኃላ ነው የኬኒያው ፕሬዚዳንት የሶማሊያ አቻቸውን ኬኒይን እንዲጎበኙ ይጋበዙት ይህ የሚያስየው ሁለቱን ወገኖች ኬኒያ መንቀሳቀስ መጀመሮን ነው እያሉ ነው የኬንያ ማመገናኛብዙሀን።

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ ረቡዕ የካቲት 19ቀን2024   የሁለት ቀን ይፋዊ የስራ ጉብኝት ናይሮቢ ጆሞ ኬንያታ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኬንያው ምክትል ፕሬዝዳንት ሪጋቲ ጋቻጓ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የኬንያ የዜና ምንጮች የሃሰን ሼክ ናይሮቢ መምጣት ከስድስተኛው የተባበሩት መንግስታት የአካባቢ ጥበቃ ጉባኤ (UNEA6) ጋር ተያይዘዋል።

የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስብሰባ ጎን ለጎን የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ፊት ለፊት እገናኝተው ሊያደራድሩዋቸው ስለማቀዳቸው እስካሁን የተገኘ ይፋዊ መረጃ የለም።  ሶማሊያ ከሶማሌላንድ ጋር የተደረሰውን ስምምነት ከማፍረሱ በፊት ከኢትዮጵያ ጋር ለሽምግልና “ቦታ” እንደማይኖር ስትገልጽ ቆይታለች – የሶማሊያ ተገንጣይ ግዛት ከሰላሳ ዓመታት በላይ ቆይቷል።

በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል ሊኖር ስለሚችል ወታደራዊ ግጭት መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ አካላት ስጋታቸውን እየገለጹ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ውጥረት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ በርካታ መንግስታት እያሳሰቡ ነው።

LEAVE A REPLY