ኢትዮጵያ ነገ ዜና:- በአዲስአበባ በአፍሪካ አዳራሽ እና በኢዬቤልዩ ቤተመንግስት መሃል በሚገኝው የመንገድ አካፋይ መናፈሻ ውስጥ የቆመው የአርቲስት አጫሉ ሁንዴሳ እንደሆነ የሚነግርለት ሀውልት የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን እያነጋገረ ነው።
ሐውልቱ ከዛሬ ሃያ ሰባት አመት በፊት ከቆመበት የተገረሰሰው የሌኒን ሐውልት ቆሞበት ከነበረበት አማካይ ቦታ ፈረስ ላይ ተቀምጦ የሚያሳይ ሐውልት ሲሆን እስከአሁን ሐውልቱ ሳይገልፅ ተሽፍኖ ነው ያለው።
ከአንድ አመት በላይ ተሽፍኖ የሚገኝው የአርቲስት አጫሉ ሁንዴሳ ሀውልት እንደሆነ የሚነገርለት ይሄ ሀውልት የቆመበት ስፍራ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት መስራች የአፍሪካሀገር መሪዎች የተከሉዎቸው የመታሰቢያ ዛፎች የሚገኙበት መናፈሻ ውስጥ ነው።
መናፈሻውን ታሪካዊነቱን እንደጠበቀ በርካታ ሚሊዬን ብር ኢንቨስት አድርገው ሼህ አላሙዲ እልምተውት ለአመታት ዝግ ሆኖ ከቆየ በኃላ ክፍት ተድርጎ እገልግሎት እየሰጠ ነውና በዚህ ኢትዮጵያ ፓርክ አፍሪካ ፓርክ በሚል ስያሜ ተሰጥቶት አገልግሎት እየሰጠ ያለው መናፈሻ ሰሞኑን እየታደሰ ነው። በከተማው መናፈሻዎችን ፓርኮችን እና የመንገድ እካፋይ ደሴቶችን አደባባዬችን የሚያስተዳድረው ቢሮ ስለ ሀውልቱ የማን እንደሆነ ማን እንዳሰራው መረጃ ለመስጠት ፍቃደኛ አይደለም።
የደጎል አደባባይ የፑሽኪን ሀውልት የሜክሲኮ እደባባይ የሰዎች ለስዎች ድርጅት መስራች የካርል ሀውልት ያለምንም የህዝብ ማስታወቂያ አፍርሶ እስወግዶ ያለው የአዲስ አበባ መስተዳድር የአርቲስት አጫሉ ሁንዴሳን የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ምስራቾች መታሰቢያ ውስጥ በምን አግባብ እንደአቆመው ሊያሰውቅ ይገባል ።”ሲሉ ለኢትዮጵያ ነገ እስተያየት የሰጡ የከተማው ነዋሪዎች ተናግረዋል ።