የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ነዋሪ ለአካባቢው ዘብ እንዲቆም ተጠየቀ

የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ነዋሪ ለአካባቢው ዘብ እንዲቆም ተጠየቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና :- የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ነዋሪ ለአለፉት ሃያ ሰባት አመታት ሲፈፀምበት የነበረው ግፍ እና በደል እንዳይመለስ በየአካባቢው ሰላሙን ለመጠበቅ ዘብ እንዲቆም ተጠየቀ።
    የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እና የሠላምና ደህንነት መምሪያ ኃላፊ ኮረኔል ደመቀ ዘውዱ በዞኑ በሚገኙ ዘጠኝ ማሠልጠኛ ዎች ገብተው የስለጠኑ ከዞኑ ሁሉም ወረዳዎች    የተወጣጡ ሚሊሻዎችን  ፀጥታእስከባሪዎችንየሕዝባቸውን ሰላም በማስጠበቅ በታማኝነት እና በቅንነት ሊያገለግሉ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ለሰልጣኞቹ ባደረጉት ንግግር ዞኑ ከሁለት የጎረቤት ሀገራት ጋር እንደመዋሰኑመከላከያ ሠራዊት የሀገርን ዳር ድንበር የሚያስጠብቅ በመኾኑ ሰልጣኝ ሚሊሻዎች  ሕገ ወጥ የሰዎችን ዝውውር እና ሕገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎችን  በመቆጣጠር የአካባቢያችሁን ሰላም ልታስጠብቁ ይገባል  ያሉትኮረኔል ደመቀ ዘውዱ ሰልጣኞች በስልጠናው ያገኙትን እውቀትና ልምድ  ተጠቅመው ለበለጠ ተልእኮ እንዲዘጋጁ እሳስበዋል።
    በስልጠናው ማጠናቀቅያ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉትየወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አሸተ ደምለው  “ሀገር ወዳድ የተከዜ ልጆች ዛሬም የሀገራቸውን አንድነት እና ሰላም ያስጠብቃሉየተከዜ አዳኝ ዘቦች የጸጥታ አካላት የአካባቢያቸውን ሰላም ከማስጠበቅ በተጨማሪ የሀገራቸውን ሉዓላዊነት እና አንድነት አስጠብቀው ይዘልቃሉ ነው ያሉት። ሁሉም የዞኑ ህዝብ ለአካባቢው ሰላም መከበር እና ለሀገሩ ዘብ የመሆን ታሪክ ያለው መሆኑን ዳግም እንደሚያስመሰክር እምነታቸው መሆኑን ተናግረዋል።

LEAVE A REPLY