* በግብጽ እርዳታ የተገነባው ግዙፍ ግድብ ይመረቃል!!!
ኢትዮጵያ ነገ ዜና :- በቀጣዩ ሳምንት መጨረሻ በታንዛኒያ ዋና ከተማ ዳሬሰላም የግብፁ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አይሲሲ እና የኢትዮጵያው ጠቅላይሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ይገናኛሉ ተባለ።
የኢትዮጵያ ነገ ዘጋቢ ከዳሬሰላም ዲፕሎማቶችን በመጥቀስ እንደዘገበው የግብፅ መንግስት ከታችኛው የናይል ተፋሰስ ሀገሮች ጋር የወንዙን ውሃ በፍህታዊነት ለመጠቀም እየሰራሁ ነው ለማለት የሚያስችል የፕሮፓጋንዳ ሥራ በማካሄድ ላይ ነው።
በቀጣዩ ሳምንት መጨረሻ በታንዛኒያ ሁለቱ መሪዎች የሚገናኙት የግንባታ ሥራው በ2019 ተጀምሮ በያዝነው 2024 የተጠናቀቀው የሀይድሮ ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ጣብያ እና ግድብ የምረቃ ስነ ስርአት ላይ እንደሚታደሙ ነው ምንጮች ለዘጋቢያችን የገለፁት።
የታንዛንያ መንግስትምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርእና የኢነርጂ ሚኒስትር ዶቶ ቢቲኮ ለዜና ሰዎች እንደገለጹት የጁሊየስ ኔሬሬ የውሃ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ተጠናቆ ኃይልመስጠት በይፋ የሚጀምርበት የምረቃ ስነስርአት ላይ የግብፅ ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ ኤል-ሲሲ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ርዕሰብሔሮች ይገኛሉ።
የታንዛኒያ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሉ ሀሰን ጋባዥነት እና የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንስትርም ታንዛንያን በይፋ ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ግንባታው በ 2019 የጀመረው በታንዛኒያ የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት ጁሊየስ ኔሬሬ የተሰየመው የግድብ ግንባታ እና የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣብያ ፕሮጀክቱ በ 2.9 ቢሊዮን ዶላር ወይንም (6.6 ትሪሊዮን የታንዛንያ ሽልንግ) አጠቃላይ ወጭ በግብፅ መንግስት የገንዘብ ብድር እና እርዳታ በግብፅ የኮንስትራክሽን ኩባንያዎች ፣ በአረብ ኮንትራክተሮች እና በኤልሲድብሊው ሰልፍ ኤሌክትሪክ ኅይል ማመንጫ ጣብያ ግንባታ ኩባንያዎች ጥምረት እየተገነባ ነው።
በዚሁ ግዙፍ ግድብ ላይ በተገጠሙ ስምንት ተርባይኖችበማንቀሳቀስ 235 ሜጋ ዋት የኤሌትሪክ ኅይል ውደ ለብሔራዊ የኤሌክትሪክ ቆት ያቀርቧል። ተብሎ እንደሚጠበቅ ታውቋል ።