ኢትዮጵያ ነገ ዜና :- በስድስተኛው የተመድ የአካባቢ ጥበቃ ጉባዔ ላይ የግብፅና የቱርክ መንግስታት ተወካዬች አለምአቀፉ መኅበረሰብ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጫና ያደርግበት ዘንድ ጥሪ ማቅረባቸው ተሰማ።
ምንጮች እንደገለጹት ግብፅና ቱርክ የኢትዮጵያ መንግስት የሶማሊያን ሉዐላዎነት በመጣስ ሐርጌሳ ላይ መንግስት መስርቻለሁ ከምትለው ሶማሌላንድ ጋር የባህር በር ወድብ ለመገንባት እና የጦር ሰፈር ለመመስረት ስምምነት መፈራረምዋን አስመልክቶ ነው አለምአቀፉ ማህበረሰብ ጫናና ውግዝት እንዲያደርግባት ዘመቻ እያካሄዱባት መሆኑን
የገለፁት።
ሰኞ የካቲት 18ቀን 2016 በተጀመረው ስድስተኛው የተመድ የአካባቢ ጥበቃ ጉባዔ ላይ ከ193 ዓለም አገራት የተውጣጡ ከ5 ሺህ በላይ የልዑካን ቡድን አባላት የ53 የአገራት መሪዎች እንዲኹም የሲቪል ማኅበራት እና የግሉ ዘርፍ ተወካዮች በሚሳትፉበት ለአምስት ቀናት በሚካሄደው ጉባዔ ላይ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድም ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በቀጣዩ ዓርብ የካቲት 22ቀን 2016 ይጠናቀቃል ተብሎ በሚጠበቀው ጉባኤ ላይ የሶማሊያ ፌደራል ሪፕብሊክ መንግስት ተወካዬችም የኢትዬጵያ መንግስት ለሉዐላዊ ግዛታቸው እና ለዘላቂ ሰላማቸው ስጋት መሆኑን በመግለፅ ላይ መሆናቸውን ምንጮች ለኢትዮጵያ ነገ ገልፀዋል