ሻምፒዮናውን ኢትዮጵያ ከአፍሪካ 1ኛ በመሆን አጠናቃለች

ሻምፒዮናውን ኢትዮጵያ ከአፍሪካ 1ኛ በመሆን አጠናቃለች

በስኮትላንድ ግላስጎው በተካሄደው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በሴቶች 1 ሺህ 500 እና 800 ሜትር ሩጫ የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች። 

በሻምፒዮናው አትሌት ጽጌ ዱጉማ በሴቶች 800 ሜትር ውድድር 2:01.90 በሆነ ሰዓት በመግባት የወርቅ ሜዳልያ አስገኝታለች።

በሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር ፍፃሜ ውድድር ደግሞ ፍሬወይኒ ኃይሉ 4:01.46 በሆነ ሰዓት በመግባት የወርቅ ሜዳልያ አምጥታለች። 

በ19ኛው የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ 2 ወርቅ፣ 1 ነሀስ እና 1 ብር በአጠቃላይ በአራት ሜዳሊያዎችን በማግኘት ከአፍሪካ 1ኛ ከዓለም 5ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች።

LEAVE A REPLY