በባሕር ዳር ከተማና በዙሪያው ውጥረት እንደነገሰ ነው!

በባሕር ዳር ከተማና በዙሪያው ውጥረት እንደነገሰ ነው!

በርካታ የከተማው ነዋሪዎች እየታሰሩ ነው

ባለፈው ሐሙስ ንጋት ላይ አንስቶ በባሕር ዳር ከተማ እና በዙሪያው ተከስቶ የነበረው የተኩስ ልውውጥን ተከትሎ የተፈጠረው ውጥረት አሁንም እንዳልረገበ የከተማዋ ነዋሪዎች ለኢትዮጵያ ነገ ገለፁ።

በከተማው እና በዙሪያው የፋኖ ታጣቂዎችና የመንግስት የፅጥታ ኃይሎች ጋር ለሰአታት የተካሄደው የተኩስ ልውውጥን ተከትሎ በከተማው የትራስፖርት አገልግሎት ተቋርጦ እንደነበር ዛሬ ሰኞ የካቲት 25ቀን2016 በአንፃራዊነት የትራንስፖርት አገልግሎቱ መጀመሩን የተናገሩት የከተማው ነዋሪዎች ይሁን እንጂ በከተማው ዋና ዋና መንገዶች ላይ ወታደሮችን የጫኑ መኪናዎች በብዛት ሲንቀሳቀሱ እንደሚታዩ ነዋሪዎች ለኢትዩጵያ ነገ  ተናግረዋል ።

ግጭቱን ተከትሎ በሁሉም የከተማዋ ወረዳዎች የክልሉ ፖሊስ እና የመከላከያ ሰራዊት አባላት ቤት ለቤት ፍተሻ ሲያካሂዱ እንደነበረና በርካታ የፋኖ ታጣቂዎችን ይደግፋሉ ተብለው የተጠረጠሩ የከተማው ነዋሪዎች መታሰራቸውን ነዋሪዎች ለኢትዬጵያ ነገ ተናግረዋል ።

ሐሙስ የካቲት21ለአርብ አጥቢያ በባህርዳር ከተማና በዙሪያዋ ለሰአታት የዘለቀ የተኩስ ልዉዉጥ በመካሄዱ በከተማው ንግድ ቤቶች ለቀናት ዝግ ሆነው እንድነበር እና ዛሬ ሰኞ የካቲት 25ቀን 2016 ተከፍተው አገልግሎት መስጠት ቢጀምሩም በከተማው የነገሰው ውጥረት አሁንም እንዳልተወገደ እንቅስቃሴውም እጅግ ቀዝቃዛ መሆኑን የአይን እማኞች ለዘጋቢያችን ገልፀዋል ።

የባሕርዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አባላትም በከተማዋ ቤት ለቤት በመዘዋወር በከተማው ተፈጥሮ የነበረውየጸጥታ ችግር ወደ ሰላማዊ ሁኔታ ተመልሷል።ስለዚህ ልጆቻችሁን ወደ ትምህርት ቤት ላኩ የተዘጉ የንግድ ቤቶችም ክፍት ሆነው ስራ እንዲጀምሩ ሲያሳስቡ እንደነበር የከተማው ነዋሪዎች ለኢትዮጵያ ነገ ዘጋቢ ተናግረዋል።

በአርብ ንጋት ላይ በባህርዳር ከተማና በዙሪያዋ ሲካሄድ በነበረው ድንገተኛ የተኩስ ልውውጥነዋሪዎችን አስደንግጦ ለከፍተኛ ስጋት መዳረጉን ተከትሎ  የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ተቋርጦ ነበር፤ የንግድ ቤቶችም  ለሁለት ቀናትተዘግተው ነበር የካቲት 24/2016 ዓ.ም አመሻሽ ጀምሮ ግን የትራንስፖርት አገልግሎት ሥራ ጀምሯል ያሉት።  የባሕርዳር ከተማ ነዋሪዎች  አሁንም በከተማው ከፍተኛ ውጥረት መንገሱንና ለኢትዮጵያ ነገ ተናግረዋል

LEAVE A REPLY