ኢትዮጵያ በወራሪው የሶማሊያው የሲያድ ባሬ መንግሥት የተቃጣባትን ጥቃት የመከተችበት የካራማራ ድል 46ኛው ዓመት የድል በዓል ዛሬ የካቲት 26ቀን2016 በድላችን ሐውልት ( ኢትዮ ኩባ የወዳጅነት አደባባይ) ውስጥ ተከብሯል።
በዚህ ሥነ ሥርዓት ላይ በወቅቱ በጦርነቱ ላይ ጉልህ የጦር ጀብዱ የፈፀሙ ጀኔራል መኮንኖች ተገኝተዋል ። በበዓሉ ላይ በጦርነቱ ወቅት ከኢትዮጵያ ጎን ተሰልፈው የተዋጉ ኩባውያንና በኢትዮጵያ የኩባ አምባሳደርም በመታስብያ ስነስርአቱ ላይ ተገኝተዋል ።
አያሌ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችም የታደሙበት ይህው የካራማራ ድል መታሰቢያ ስነስርአት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያ በየዓመቱ በድምቀት በመከበር ላይ ነው።