በአንድ ወር 300ሚሊዮን ለመስብሰብ ታቅዷል
መጋቢት 24 ቀን 2016 ዓ.ም የመሰረት ድንጋይ ተጥሎ ግንባታው የተጀመረው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ አስራሶስተኛ አመቱን ይይዛል ።
ይህንንም ተከትሎ በቀጣዬቹ 30ቀናት ሦስት መቶ ሚሊዮን ብር ገንዘብ ለማሰባሰብ መታቀዱንየህዳሴግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ፅህፈት ቤት ዕሮብ የካቲት 27 ቀን 2016 ዓ.ም ጥሪ አደረገ።
የፅሕፈት ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ፍቅርተ ታምር፤ የግድቡ አጠቃላይ አፈፃፀም 95 ፕርሰንት መድረሱን የሲቪል ሥራው 98 በመቶ እንዲሁም የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራው 78 በመቶ መድረሱን አሁን ላይ ሁለት ተርባይኖች ኃይል እያመነጩ ሲሆን በቀጣይም ሌሎች ተርባይኖች እንደሚጀምሩ ተናግረዋል ።
ግድቡ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስከ አሁን በሕዝብ ተሳትፎ 18 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር መሰብሰቡንም ገልፀዋል።
ህብረተሰቡ ፍፃሜውን ለማየት በጉጉት እየጠበቀ ሲሆን ይህ ብሄራዊ ፕሮጀክት ተጠናቆ አስራሶስቱም ተርባይኖች ኃይል ማመንጨት የሚጀምሩት መቼ ነው የሚለውን ጥያቄ የሚመልስ አካል የለም።
መንግስት የተለያዩ የቱሪስት መዳረሻዎች ናቸው ያላቸውን ግንባታዎች አጠናቆ ወደ ሥራ ለመግባት ያሳየውን ቁርጠኝነት ለምን በህዳሴው ግድብ ፕሮጀክት ላይ ሊያሳይ አልፈለገም ሲሉ የሚጠይቁ በርካታ እስተያየት ስጭዎች አሉ።