ኢትዮጵያ ነገ ዜና || “ሁከት እና በጥብጥ በማነሳሳት” ወንጀል ተጠርጥረው ላለፉት 13 ቀናት በእስር ላይ የቆዩት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የፖለቲካ ኦፊሰር አቶ በቴ ኡርጌሳ፤ 100 ሺህ ብር የዋስትና ገንዘብ በማስያዝ ጉዳያቸውን በውጭ እንዲከታተሉየአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ ችሎት ነው።
አቶ በቴ ኡርጌሳ “አፍሪካ ኢንተለጀንስ” ለተሰኘው የዜና ድረ ገጽ ዘጋቢ ከሆነው ፈረንሳዊ ጋዜጠኛ አንቷን ጋሊንዶ ጋር ሐሙስ የካቲት 14፤ 2016 በአዲስ አበባው ስካይ ላይት ሆቴል በውይይት ላይ በነበሩበት ወቅት ነው በፀጥታ ሰራተኞች በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩት ፈረንሳዊው ጋዜጠኛ ባለፈው ሳምንት ከእስር ተፈቶ ከሃገር ሲወጣ በቴ ኡርጌሳ ለሶስተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀረበው በፖሊስ ተደጋጋሚ የጊዜ ቀጠሮ ሲጠየቅባቸው ቆይቷ ዛሬበ100ሺህ ብር ዋስትና እስይዞ እንዲፈታ የተወሰነለት።
የካቲት 27/2016 ረፋዱን የተስየመው የአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ ችሎት ተከሳሽን በተመለከተ በቁጥጥር ስር ያዋለው
ፖሊስ “ምርመራዬን አልጨረስኩም” በሚል ተጨማሪ 11 የምርመራ ቀናትን ጠይቋል። የአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ባለፈው ሳምንት ሐሙስ በነበረው ችሎት ለፖሊስ ተጨማሪ አምስት የምርመራ ቀናት የፈቀደው፤ ፖሊስ የሚያቀርበውን “የስልክ ምርመራ ውጤትን ለመስማት” ነበር።
በዛሬው ችሎት የተገኙት መርማሪ ፖሊስ፤ የአቶ በቴን የስልክ የምርመራ ውጤት ለመቀበል ለኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢንሳ) በተደጋጋሚ ጥያቄ ምማቅረባቸውን ሆኖም እስካሁን ውጤቱን አለመቀበላቸውን ገልጸዋል። ከዚህ በተጨማሪም የሰው ማስረጃ ለማሰባሰብ ተጨማሪ ቀናት እንደሚያስፈልጓቸው አስረድተዋል። የችሎቱ ዳኛም ተለዋጭ ቀጠሮ ከመስጠታቸው በተጨማሪ የእንድመቶ ሺህ ብር ዋስ ጠርቶ እንዲወጣ ለአቶ በቴ ኡርጌሳን ዋስትና ፈቅዶለትል።