ከ 200 የሚበልጡ የትግራይ ተወላጅ የቀድሞ ወታደሮች በእስር ላይ ናቸው ተባለ

ከ 200 የሚበልጡ የትግራይ ተወላጅ የቀድሞ ወታደሮች በእስር ላይ ናቸው ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በየካቲት ወር አጋማሽ ላይ    በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር  ምክትል ፕሬዝዳንት በጀኔራል ታደሰ ወረደ ለመከላከያ ሚኒስትር በጻፉት ደብዳቤ  220 የትግራይ የቀድሞ ወታደሮች በወታደራዊ ፍርድ ቤት ከተከሰሱ በኋላ በእስር እንደሚገኙ አስታውቀዋል።

ከመኮንኖቹ ውስጥ ሰባቱ የዕድሜ ልክ እስራት ፣ 14 ቱ ከ 15 እስከ 25 ዓመት የሚደርስ ቅጣት እና ሌሎች ደግሞ አጭር የእስር ቅጣት ተጥሎባቸው በእስር ላይ እንደሚገኙ ተመልክቷል።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝደንት ለሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በፃፉት ደብዳቤ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ታስረው የሚገኙትን 220 የታሰሩ የትግራያን የቀድሞ ወታደሮች እንዲፈቱ ጠይቀዋል።

እነዚህ መኮንኖች ከጦርነቱ ጋር በተያያዙ ውንጀላዎች ጥፋተኛ እንደሆኑ የተገለፀ ሲሆን ይህ ደግሞ በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መፍትሄ አግኝቷል።  የሰላም ስምምነቱን በህዳር 2022 በመፈረም በትግራይ መሪዎች እና በወታደራዊ ባለስልጣናት ላይ ክስ ውድቅ አድርጓል። “የእነዚህ ግለሰቦች መታሰር ከፕሪቶሪያ ስምምነት መንፈስ ጋር የሚቃረን እና ብሄራዊ እርቅ እና የሰላም ግንባታ ጥረቶችን እንቅፋት ይፈጥራል” ሲል ለመከላከያ ሚኒስትሩ የተላከው ደብዳቤ አስታውሶ፤  በይቅርታ ወይም በምህረት ቢለቀቁ እርምጃው  የፌዴራል መንግስቱ ለሰላም ስምምነቱ ተፈፃሚነት ያለውን ቁርጠኝነት ሊያመላክት ይችላል። ብሏል።   

የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር በፃፈው ደብዳቤየኢፌድሪ መከላከያ ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው ወገኖች ጋር ተነጋግሮ ታሳሪዎችን እንዲለቀቁ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል።

ዛሬ በፕሪቶሪያው የሰላም ስምነት የአተገባበር    ሂደት ያተኮረ ተፈራራሚ አካላትና የአፍሪካ ህብረትን ያሳተፈ ግምገማ  ላይ ከመነጋገሪያ አጀንዳዎች አንዱ እንደሚሆን  ምንጮች ተናግረዋል።

ሰላም እንዲሰፍን የፕሪቶሪያ የሰላም ውል ሙሉ በሙሉ መተግበር የግድ ነው ያሉት ጊዜያዊ ፕሬዚዳንትጌታቸው ረዳ ስምምነቱ ሕግና ሕገ-መንግስታዊ የትግራይ ህዝብ ጥያቄዎችን ባከተተ መልኩ መገምገም አለበት ብለዋል።

የአፍሪካ ህብረት የፕሪቶሪያው የሰላም የስምምነት መሬት ላይ እንዴት እየተፈፀመና እየተተገበረ  አንደሆነ አስመልክቶ  በጀመረው ስትራቴጂክ ግምገማ ከስምምነቱ ፈራሚዎች በተጨማሪ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፣ የአውሮፓ ህብረት ፣ ኢጋድ እና አሜሪካ  ተወካዮች ይገኛሉ።

LEAVE A REPLY