ግብፅ የሱዳን ፖለቲከኞችንእያሰባሰበች ነው

ግብፅ የሱዳን ፖለቲከኞችንእያሰባሰበች ነው

እብዱል ፈታህ እይሲሲ በሱዳን ሰላም ለመምጣት እየጣሩ ነው 

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የሱዳን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ  የጸረ-ጦርነት ጥምረት “ታጋዱም” መሪ የግብፅ መንግስት   በሱዳን እየተካሄደ ያለውን ጦርነት ማቆም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ለመምከር ካይሮን እንዲጎበኙ ይፋዊ ግብዣ ቀረበላቸው።

የታጋዱም ባለስልጣናት ግብዣውን ማክሰኞ የካቲት 26/2016 ማግኘታቸውን እና የሃምዶክን ጉብኝት ለሚቀጥለው ሳምንት ለማዘጋጀት እየሰሩ መሆናቸውን ለሱዳን ትሪቡን አረጋግጠዋል። 

ከግብፅ አመራሮች ጋር በሚደረገው ውይይት ላይም ከጥምረቱ የተውጣጡ ከፍተኛ የልዑካን ቡድንን ይመራሉ     ተብሎ ይጠበቃል።

ጉብኝቱ ታጋዱም ከጦር ኃይሎች መሪዎች ጋር ለመወያየት ባቀደው የፍኖተ ካርታ ላይ ለመወያየት ሲፈልግ እና በመጨረሻም ከአዲስ አበባ መግለጫ ጋር የሚመሳሰል የመርሆዎች መግለጫ በመፈረም ከፈጥኖ ደራሹ ኃይሎች (አርኤስኤፍ) መሪ መሃመድ ሃምዳን ጋር ተፈራርመዋል። 

ዳጋሎ “ሄሜቲ” እናፀረ-ጦርነት ሃይሎች ከሱዳን ወታደራዊ መሪ አብደል ፈታህ አል-ቡርሃን ጋር በፍኖተ ካርታቸው ላይ ለመወያየት ጥያቄ ቢያቀርቡም ቀንና ቦታ እስካሁን የተረጋገጠ ነገር የለም።

የታጋዱም ቃል አቀባይ አላ ኤል-ዲን ኑቁድ ለሱዳን ትሪቡን እንደተናገሩት ጉብኝቱ በመጀመሪያ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም የግብፅ ፕሬዝዳንት ከረመዳን በፊት እንዲደረግ ሀሳብ አቅርበዋል ።  የተወሰነው ቀን በቅርቡ እንደሚረጋገጥም አክለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአፍሪካ ኅብረት የሱዳን ከፍተኛ የፓናል ቡድን ከቀድሞው እስላማዊ አገዛዝ የተበታተነውን ናሽናል ኮንግረስ ፓርቲ (ኤንሲፒ) ተወካዮችን ትናንት ካይሮ ላይ አወያይቷል።

ይህ የአፍሪካ ህብረት የሱዳን ከፍተኛ የፓናል ቡድኑ ቀጣይነት ያለውን ግጭት ለማስቆም ከተለያዩ የሱዳን የፖለቲካ ቡድኖች ጋር ለመነጋገር እያደረገ ያለው ጥረት አካል መሆኑ ተገልፃል።

LEAVE A REPLY