ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በኢትዮጵያ መንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ጥቃት እንደተፈጸመባቸው በዚህ ምክንያት ከሀገር ወጥተው የነበሩት የአፍሪካ ልማት ባንክ የምሥራቅ አፍሪካ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱል ካማራ፤ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ተገናኝተዋል።
ሚኒስትሩ የማክሮ ኢኮኖሚ አማካሪ አምባሳደር ግርማ ብሩ በተገኙበት በተካሄደ ስነስርአት የመታሰቢያ ስጦታ ተበረከተላቸው።
በጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሳንዶካን ደበበ አቅራቢነት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለዶ/ር አብዱል የአንገት ሀብል ሲያበረክቱላቸው የሚያሳይ ሌላ ፎቶ በመኃበራዊ ሚዲያ ገፃች ሲዘዋወር ውሎል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ለዶ/ር አብዱል ያጠቁላቸው ሀብል የኢትዮጵያ ካርታ የተቀረጸበት ሲሆን ሀብሉ የተበረከተላቸው የአፍሪካ ልማት ባንክ የምሥራቅ አፍሪካ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱል፤ ባለፈው ኅዳር ወር ላይ በኢትዮጵያ መንግሥት የፀጥታ ኃይሎች እስር እና አካላዊ ጥቃት ከደረሰባቸው የባንኩ ሠራተኞች አንዱ እንደሆኑ የኬንያው “ዴይሊ ኔሽን” ጋዜጣ ዘግቦል ዶ/ር አብዱል የደረሰባቸውን ጥቃት የሚያሳይ ፎቶም በማኅበራዊ ትስስር ገጾች ሲዘዋወር ነበር።
የባንኩ ሠራተኞቹ ላይ በተፈጸመው “ከሕግ ውጪ” የሆነ እስር እና አካላዊ ጥቃት ምክንያት ዓለም ዓቀፉ ድርጅት ሠራተኞቹን ከኢትዮጵያ አስወጥቶ ነበር ።
ባለፈው ጥር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በኢትዮጵያ መንግሥት ስም በባንኩ ሠራተኞች ላይ ለደረሰው አካላዊ ጥቃት እና የዲፕሎማሲያዊ መብት ጥሰት “መደበኛ ይቅርታ” በማቅረባቸው ሠራተኞቹን ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ መወሰኑን ይታወሳል።
በስነ ስርአት ላይ ጠቅላይ ሚንስትሩ “ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር ያላት አጋርነት ውጤታማ ሆኖ ቀጥሏል” ያሉት ዐቢይ፤ ከዶ/ር አብዱል ጋር የነበራቸው ውይይት ባንኩ “በኢትዮጵያ በሚያካሂዳቸው ፕሮጀክቶች” ላይ ያተኮረ እንደሆነ ገልጸዋል። የሽልማት ስነ ስርአቱን በተመለከተ እስተያየት የሰጡ ስማቸው እንዳይገለፅ የጠየቁ ዲፕሎማት ጠቅላይሚንስትሩ ለዳይሬክተሩ በካሳ መልክ ያደረጉት ሀብል ይልቅ ጥቃቱን በፈፀሙ የፀጥታ ሰራተኞችንላይ እርምጃ መውሰዳቸውን ቢያስውቁ ይሻል ነበር ብለዋል።