በመላ አገሪቱ ለሀያ ቀናት የመንገድ የትራፊክ ቁጥጥር  ሊካሄድ ነው 

በመላ አገሪቱ ለሀያ ቀናት የመንገድ የትራፊክ ቁጥጥር  ሊካሄድ ነው 

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ለቀጣዬቹ ሃያ ቀናት በክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች መውጫ በሮች  በሞተር ሳይክል አገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም ዓመታዊ የተሽከርካሪ ቦሎ ያላደረጉና ሦስተኛ ወገን መድን ሽፋን የሌላቸው ተሸከርካሪዎች ላይም የተጠናከረ ቁጥጥር  እንደሚካሄድ ተገለፀ።

ከተፈቀደላቸው የጭነት ልክ በላይ የሚጭኑና በተሸከርካሪዎቻቸው ላይም በሚታዩ ግልጽ የቴክኒክ ጉድለቶች ላይም ቁጥጥር እንደሚደረግና መርኃ ግብሩ  አዘጋጅ የመንገድ ደኅንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት  አስታወቀ። 

የመንገድ ደኅንነት መድን ፈንድ ከፌዴራል ፖሊስ፣ ከክልልና ከተማ አስተዳደር የትራፊክ ፖሊስና ትራንስፖርት ቢሮዎች ጋር በመተባበር  ከመጋቢት ፮ቀን ጅምሮ እስከ መጋቢት፪፮ ቀን ፪ሺ፩፮ ቁጥጥሩ በሀገሪቱ በመላ ይካሄዳል ተብሏል።

የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጀማል አባሶ  በሰጡት መግለጫ መርኃ ግብሩ በዋናነት በአገር አቀፍ ደረጃ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት እያስከተለ ያለውን የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ ያለመ ነው ብለዋል። 

በተያዘው በ2016 በጀት ዓመት በመጀመሪያው ስድስት ወራት በትራፊክ አደጋ 1 ሺህ 358 የሞት፣ 2 ሺህ 672 ከባድና 2 ሺህ 401 ቀላል የአካል ጉዳት የተመዘገበ ሲሆን ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት መውደሙን መረጃዎች ያመለክታሉ። en

LEAVE A REPLY