ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በሶማሌ ክልል የታሰረውን ጋዜጠኛ ሙህያዲን መሀመድ አብዱላሂን አስመልክቶ ትናንት ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋዜጠኞችን በዘፈቀደ ከማሰር ሊቆጠቡ ይገባል ብሏል።
ከአንድ ወር ገደማ በፊት የታሰረውን ጋዜጠኛ ሙህያዲን መሀመድ አብዱላሂን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ኮሚቴ ሲፒጄ ጠይቋል።
ሙክሲየዲን ሾው፤ በሚል የፌስ ቡክ ገፁ ላይ ዘገባዎችን እና አስተያየቶችን የሚጽፈው ሙህያዲን፤ በኢትዮጵያ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መዲና ጅግጅጋ፤ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ በፀጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ስር መዋሉን ኮሚቴው አመልክቷል።
በጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር መጋቢት 4 ቀን ሙህያዲን የኢትዮጵያን የጥላቻ ንግግር እና የሀሰት መረጃ ህግን በመጣስ እና የሀሰት ዜና እንዲሁም የጥላቻ ንግግር በማሰራጨት ክስ ተመስርቶበታል። የጋዜጠኛው የክስ መዝገብ እንደሚያሳየው ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ እስከ አምስት አመት እስራት ሊያስቀጣው ይችላል ሲል ሲፒጄ አስታውቋል።
ሙህያዲን በጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር የካቲት 12/2024 ቀን «ህዝቡን በፌስቡክ ገፁ ላይ በማነሳሳት» የተከሰሰ ሲሆን፤ ሲፒጄ በጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር መጋቢት 5 ቀን/2024 በጋዜጠኛው የፌስቡክ ገጽ አደረኩት ባለው ግምገማ የካቲት 11 ቀን ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጉብኝት አንድ ቀን ቀደም ብሎ ጅግጅጋ ውስጥ የተዘጉ መንገዶችን የሚተች ጽሁፍ ማጋራቱን አስታውቋል።
ይህም የትራንስፖርት ዋጋ ጨምሯል እና መንግስት ህብረተሰቡን “ድሆችን መንከባከብ አለበት” የሚል ነገር ግን በክሱ ውስጥ የተጠቀሱትን ሀረጎችን ያልያዘ መሆኑን አመልክቷል።
የጋዜጠኛውን ጉዳይ በተመለከተ ሲፒጄ ከክልሉ ባለስልጣናት መረጃ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አለመሳካቱን አመልክቷል።
ሲፒጄ ታህሣሥ 1፣ 2023 ባደረገው የጋዜጠኞች እስር ቆጠራ ኢትዮጵያ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት በከፋ ሁኔታ ጋዜጠኞችን በማሰር ሁለተኛዋ ሀገር ነች ብሏል። en