ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት የሽግግር ተልእኮ ስር የሚገኘው የጅቡቲ ጦር በሂራን ክልል ዋና ከተማ በለደዎይን የሚገኘውን ትልቅ የጦር ሰፈር ትናንት ለቀው ወጥተዋል።
የጅቡቲ ወታደሮች የወጡት በአካባቢው ተቀናቃኝ ሃይሎች በመኖራቸው ነው።
ወታደሮቹ ቦታውን ለቀው ከመውጣታቸው በፊት በከተማዋ ከ10 ዓመታት በላይ ሰፍረው ቆይተዋል።
አንደኛው ተቀናቃኝ ሀይል የሂርሻቤሌ ክልል አስተዳደር ደጋፊ ሲሆን ፤ሁለተኛው ደግሞ ሂራብ ግዛት ተብሎ ከሚጠራው ተቃዋሚ ታጣቂ ቡድን ጋር በመተባበር ከአካባቢው ሃይሎች ጋር ፖለቲካዊ አለመግባባት ውስጥ መግባታቸው ተዘግቧል። en