ምክር ቤቱ የአቶ ክርስቲያን ያለመከሰስ መብት አነሳ 

ምክር ቤቱ የአቶ ክርስቲያን ያለመከሰስ መብት አነሳ 

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (የአብን) አመራር የአቶ ክርስቲያን ታደለ ፀጋዬን ያለመከሰስ መብት አነሳ 

ምክር ቤቱ በዛሬው እለት የአቶ ክርስቲያን ታደለን ያለመከሰስ መብት ያነሳው በ17ኛ መደበኛ ስብሰባው ላይ ነው።

የምክር ቤት አባሉ ያለመከሰስ መብት ተነስቶ ክስ ማቅረብ እንዲቻል ጥያቄ ያቀረቡት የፍትህ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር)÷ አባሉ መንግስታዊ ስርዓትን በሃይል ለመናድ በአማራ ክልል ለሚንቀሳቀስ ቡድን መመሪያ ሲሰጡ እንደነበር ገልጸዋል። 

“የምክር ቤት አባሉ ለእስር ከተዳረጉ ከሰባት ወራት በላይ ተቆጥረው ሳለ፣ አሁን ያለመከሰስ መብታቸውን ማንሳት ለምን አስፈለገ”? የሚሉ ጥያቄዎችን የምክር ቤት አባላት አንስተዋል፡፡

“በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማዕቀፍ ውስጥ መደበኛው የዳኝነት ሂደት ጣልቃ መግባት እንደማይችል እየታወቀ፣ ሂደቱን መከወን ለምን አስፈለገ” የሚሉ ጥያቄዎችም ቀርበዋል።

ምክር ቤቱም የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ካደመጠ በኋላ፣ በሁለት ተቃውሞና በሁለት ድምፀ ታቅቦ የአቶ ክርስቲያን ታደለን ያለመከሰስ መብት በአብላጫ ድምፅ አንስቷል፡፡en

LEAVE A REPLY