በሜ/ጀ ክንፈ ዳኘው እና አብዲ ኢሌ መዝገቦች ክሶች ተቋረጡ

በሜ/ጀ ክንፈ ዳኘው እና አብዲ ኢሌ መዝገቦች ክሶች ተቋረጡ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የፍትህ ሚኒስቴር በሜ/ጀ ክንፈ ዳኘው እና በአብዲ ሞሃመድ ዑመር (አብዲ ኢሌ) ክሶች ለህዝብ ጥቅም ሲባል እንዲቋረጡ መወሰኑን  ፍትሕ ሚኒስቴር አስታወቀ።

በእነ ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው መዝገብ ስር ያሉ ተከሳሾች በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሙስና ወንጀል ክስ ክርክር ሲካሄድ የነበረ መሆኑ ይታወቃል። 

በሌላ በኩል የእነ አብዲ ሞሃመድ ኡመር የክስ መዝገብ በአንደኛ የህገ-መንግስትና የሽብር ወንጀል ጉዳዮች ችሎት የክርክር ሂደት ላይ መቆየቱ የሚታወቅ ነው። 

የኢፌዴሪ ፍትህ ሚኒስቴርም ለዘላቂ የህዝብ ጥቅም ሲባል እነዚህ የክስ ሂደቶች እንዲቋረጡ መወሰኑን  አስታውቋል፡፡ en

LEAVE A REPLY