በደቡብ ኢትዮጵያ ምክር ቤት ጉባኤ ውይይት የተደረገበት የመምህራን ደሞዝ አለመከፈል አሁንም እልባት አላገኝም። የክልሉ መንግስት ችግሩን ለመፍታት ጥረት እያደረኩ ነው እያለ ነው።
የክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ በክልሉ የመምህራንን ደሞዝን ጨምሮ ሌሎች የፋይናንስ ወጪዎችን ለማሟላት ያልተቻለው የገቢ አሰባሰብ በሚፈለገው መጠን ባለመሠራቱ መሆኑን ተናግረዋል።
በቀጣይ የፋይናንስና የገቢ ሰብሳቢ ተቋማትን አቅም በማጠናከር የደሞዝ ክፍያን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ጥረት እንደሚደረግ ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ተናግረዋል ፡፡ en