የኤርትራ ባህር ሃይል ዋናአዛዥ በሞት ተለዩ

የኤርትራ ባህር ሃይል ዋናአዛዥ በሞት ተለዩ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ጀነራል ሁመድ ካሪካሬ የኤርትራ ባህር ሃይል አዛዥ በህመም ምክንያት በ73 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ።

 ሜጀር ጀነራል ሁመድ ካሪካሬ በ1969 እና በ1970 ዓ.ም የኤርትራን ህዝባዊ ሃይሎች ተቀላቅለው ሀገራቸውንና ህዝባቸውን በተለያዩ ኃላፊነቶች እንዲሁም የሻዕቢያ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል በመሆን አገልግለዋል።

 የኤርትራ ነፃነትን ተከትሎ ሜጀር ጀነራል ካሪካሬ የዴንካሊያ አስተዳዳሪ፣ የኤርትራ ባህር ሃይል አዛዥ እና የምስራቅ ግንባር ልማት ዘርፍ አስተባባሪ የመሳሰሉ ስራዎችን በመስራት ሀገራቸውንና ህዝቡን  ማገልገላቸውን ዜና እረፍፊታቸውን ተክትሎ የተስራጨው የህይወት ታሪካቸው ያስረዳል ።ሜጀር ጀነራል ሁመድ ካሪካሬ ከባለቤታቸውና ከአራት ልጆቻቸው አፍርተዋል።

 የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ለዓርብ መጋቢት 15 ቀን 2024ዓ.ም በ10 ሰዓት በአስመራ ይፈፀማል። en

LEAVE A REPLY