ህወሐት መግለጫ አወጣ

ህወሐት መግለጫ አወጣ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና ||  ህወሓት ከተፈረመ 16 ወራት ያለፈው ውል በከፊል መፈፀሙን፣ በርካታ የስምምነቱ ይዘቶች ደግሞ አሁንም በእንጥልጥል እንዳሉ በእፍሪካ ህብረት ስብሳቢነት ለሶስት ቀናት በተካሄደው ግምገማ ላይ መነሳቱን  ባውጣው መግለጫ እውስቶል።

    ህወሓት በስምምነቱ መሰረት ከመከላከያ ሰራዊት ውጭ የሆኑ ሐይሎች አሁንም ከትግራይ አለመውጣቸውን፣ 40 በመቶ የትግራይ ግዛት አሁንም ወደ ክልሉ አስተዳደር እንዳልገባ ማንሳቱን በመግለጫው ጠቁሟል። በዚህም አንድ ሚልዮን ገደማ የጦርነቱ ተፈናቃዮች ወደቀዬአቸው አለመመለሳቸውን አውስቷል። 

በህወሓት እና ፌደራል መንግስቱ መካከል ያሉ የተራራቁ አቋሞች ለማቀራረብ፣ ፖለቲካዊ ውይይት ጨምሮ ቀጣይ መድረኮችን ለማካሄድም ስምምነት ላይ መደረሱን ህወሓት አስታውቋል።

ህወሓት በአፍሪካ ሕብረት አዘጋጅነት ባለፈው ሰኞ በአዲስአበባ በተደረገው የፕሪቶርያ ውል አፈፃፀም ግምገማ መድረክ አስመልክቶ ትላንት ባወጣው መግለጫ፥ በውሉ መሰረት ያልተፈፀሙ ያላቸውን ጉዳዮች በመድረኩ ማንሳቱን ገልጿል። 

ከዚህ በተጨማሪ የቀድሞ ተዋጊዎች ወደ ሰላማዊ ሕይወት ለመመለስ በሚደረግ ጥረት አስፈላጊ ሀብት ባለመገኘቱ ፈተና እንደሆነ በመድረኩ ማንሳቱን የሚገልፀው ህወሓት፤ ከፌደራል መንግስት የሚጠበቅ የ2014 ዓመተምህረት በጀት አለመለቀቁ ተከትሎ ደግሞ የመንግስት ሰራተኞች እና ጡረተኞች ውዝፍ ክፍያቸውን ሳያገኙ መቅረታቸው እንዲሁም ሌሎች በርካታ ክፍተቶች መፈጠራቸውን ማንሳቱን ጠቁሟል።

ህወሓት በትላንትናው መግለጫው በፌደራል መንግስቱ ተወካዮች በኩል ከዚህ በፊት በነበሩ መድረኮች የተነሱ ነጥቦች መልሰው መነሳታቸውንም አውስቷል።

የህወሓት መግለጫ በውይይቱ የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት እና ህወሓት ለፕሪቶርያው ውል ያላቸውን ተአማኒነት በድጋሚ አረጋግጠዋል የሚል ሲሆን የተራራቁ አቋሞች ለማቀራረብ፣ ፖለቲካዊ ውይይትን ጨምሮ ቀጣይ መድረኮች ለማካሄድም በሁለቱ አካላት በኩል መግባባት ተፈጥሯል በማለት፥ አደራዳሪዎች በሚገኙበት በቀጣይ ጥቂት ወራት ውስጥ ስብሰባ ሊደረግ መስማማት ላይ መደረሱንም አክሎ ገልጿል።

en

LEAVE A REPLY