ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በሶማሌ እና አፋር ክልሎች በሚኖሩ ማህበረሰቦች መካከል ለረጅም ጊዜ የዘለቀው ግጭት በርካታ የሰው ህይወት እና የንብረት ውድመት አስከትሏል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የአስታራቂነት የሽምግልና ሂደት በሶማሌ እና አፋር ክልሎች ይህም ትብብርን እና ለተጎዱ ማህበረሰቦች የወደፊት ብሩህ ተስፋ የሚሰጥ የእርቅ ሂደትን ለማመቻቸት ሲንቀሳቀስ ቆይቶል።
በተደረገው እንቅስቃሴ ከሁለቱም ክልሎች የተውጣጡ ተወካዮችን እና የዕርቀ ሰላም ጥረቱን ሂደት የሚከታተል ገለልተኛ አካላትን ያካተተ የጋራ ኮሚቴ ተቋቁሟል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የጋራ ኮሚቴውን የመቆጣጠር ሃላፊነት ይወስዳል።
እ.ኤ.አ. የካቲት 29ቀን2016በተካሄደው ስነ ስርዓት ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼክ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋ ከሁለቱም ክልሎች የተወከሉ ተወካዮችን ከልብ ተማጽነዋል፤ ከሁከት እና ግጭት መቆጠብ አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።
በተለይ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሁለቱ ክልል ሚሊሻዎች በአወዛጋቢ አካባቢዎች ግጭት ሲፈጥሩ አልፎ አልፎ የሚከሰት ግጭት ከፍተኛ ውድመትና ጉዳት እያስከተለ መሆኑ እይዘነጋም። ይህ በእንዲህ እንዳለ ሀሙስና አርብ መጋቢት ፬እና ፭ በሁለቱ ክልል የወሰን አካባቢዎች ግጭት ማገርሽቱ ተሰምቶል።en