ኢትዮጵያ ለታንዛንያ ናለድቡብ አፍሪካ የኤሌትሪክ ኃይል ለማቅረብ እየሰራች ነው!!

ኢትዮጵያ ለታንዛንያ ናለድቡብ አፍሪካ የኤሌትሪክ ኃይል ለማቅረብ እየሰራች ነው!!

ኢትዮጵያ ነገ ዜና ||  ጅቡቲ፣ ሱዳን፣ ኬንያ፣ ለሚጠይቁት ተጨማሪ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ምላሽ ለመስጠት ዝግጅት መደረጉንና  ለታንዛንያ እና ለደቡብ አፍሪካ የኤሌትሪክ ኃይል ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።

   የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር  ኢንጅነርሃብታሙ ኢተፋ  እንደገለጹት÷ ኢትዮጵያ ያላትን የተፈጥሮ ጸጋ ተጠቅማ በምታመነጨው የኤሌክትሪክ ሃይል ሀገራት የሃይል ግዥ ለመፈጸም ከፍተኛ ፍላጎት እያሳዩ ነው። በዚህም ጅቡቲ፣ ሱዳን እና ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር በሃይል መተሳሰራቸውን ነው የተናገሩት፡፡ ከኬንያ ጋር የተደረገው የሃይል ትስስር ታንዛኒያን እንዲሁም ደቡብ አፍሪካን ጭምር የሚያስተሳስር መሆኑን መናገራቸው ታውቋል።

ሚኒስትሩ በመግለጫቸው በዚህም ኢትዮጵያ ቀጣናውን በኤሌክትሪክ ሃይል በማስተሳሰር ትልቅን ድርሻ እየተወጣች ነው።   ኢትዮጵያ እያቀረበች ያለው የኤሌክትሪክ ሃይል የሚመነጨው ከውሃ መሆኑና ይህም የአየር ንብረት ብከለት የማያስከትል በመሆኑ ተፈላጊነቱ እንዲጨምር አድርጓል ብለዋል።    

ይህንንም ተከትሎ አሁን ላይ የጎረቤት ሀገራት የኤሌክትሪክ ሃይል ፍላጎት በየዓመቱ 15 በመቶ ጭማሪ እያሳየ መምጣቱን ነው ሚንስትሩ በመግለጫቸው ያመለከቱት። en

LEAVE A REPLY