የትራፊክ ፖሊሶች  400 ዘመናዊ የቁጥጥር   ካሜራዎች ታጠቁ 

የትራፊክ ፖሊሶች  400 ዘመናዊ የቁጥጥር   ካሜራዎች ታጠቁ 

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በአዲስ አበባ የትራፊክ ፖሊሶች ዘመናዊ የሆኑ ከሰውነታቸው ጋር የሚጣበቅ ካሜራዎችን በማስታጠቅ ሥራ ላይ ማዋሉ ተገለፀ።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ከሬዲዮ ጋር የተገናኙ ከ400 በላይ ዘመናዊ ቦዲ ካሜራዎችን ለትራፊክ ፖሊሶች በማከፋፈል የትራፊክ እንቅስቃሴውን እየተከታተለ መሆኑን ተናግሯል።

የቦዲ ካሜራዎቹ ትራፊክ ፖሊሱ ባለበት አካባቢ ያለውን አጠቃላይ ሁኔታ የሚቀርጹና የተለያዩ መረጃዎችንም መዝግበው የሚያስቀምጡ መሆናቸውን ታውቋል።

ከዚህ ቀደም ለትራፊክ መጨናነቅና ተያያዥ ችግሮች መፍትሔ የሚሰጠው በሬዲዮ በሚደረግ ግንኙነት ነበር አዳዲሶቹ ቦዲ ካሜራዎች የተሽከርካሪ ሁኔታዎችን ጨምሮ ሌሎች ወንጀሎችንም ለመቆጣጠር የሚያስችሉ እና ካሜራዎቹ በቀጥታ በማዕከል የሚመሩና ቁጥጥር የሚደረግባቸው  መሆናቸው ተሰምቷል።

ካሜራዎቹ ውጤታማ ሥራ እየተሰራባቸው ነው ያሉት የካሜራዎቹን ብዛት ካሉት የትራፊክ ፖሊሶች ቁጥር ጋር ለማጣጣም የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ ነው መባሉ ተሰምቷል። en

LEAVE A REPLY